
አንድ ሰው ብቸኛውን ቢያጠቃውም፣ሁለት ከሆኑ ይመክቱታል፤በሦስት የተገመደ ገመድም ቶሎ አይበጠስም፡፡ – መክ 4፡12
ከእውነተኛ ጥሩ ትዳር የተሻለ ምንም ነገር የለም ከመጥፎ ትዳር ደግሞ የከፋ ምንም ነገር የለም፡፡ ክርስቲያናዊ ትዳር ማለት ሁለት ሰዎች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለራሳቸው ደስታ እና አለም ላይ ተጽዕኖ ፈጥሮ ለማሳካት ጠንካራ ሀይል እንደሆኑ ህያው ማሳያ ነው፡፡
ነገር ግን ሁለት ሰዎችን ወደ አንድ ትዳር ማዋሀድ በራሱ የማይሆን ሂደት ነው፡፡ስትጋቡ ምንም ያህል ጥልቅ ፍቅር ውስጥ ብትሆኑም ጥሩ ትዳር ዝም ብሎ አይመጣም፡፡ እግዚአብሔርን በሂደቱ ውስጥ መጋበዝ አለባችሁ፡፡
ኢየሱስን ስናውቀውና ወደ ትዳራችን ስንጋብዘው ግንኙነታችን በሶስት ይገመዳል፡፡ ክርስቶስ ሲጨመርበት የወንድ እና የሴት ግንኙነት እጅግ ጠንካራ ይሆናል፡፡
በትዳር ውስጥ ደስታ ማለት ሁልጊዜ እኛ እንደምንፈልገው የሚሆን የትዳር አጋር ማግኘት አይደለም፡፡ ሁለት ፍጹም ያልሆኑ ሰዎች ፍጹም በሆነ አምላክ ሲታመኑ እና ከፈቃዱ እና ከአላማው ጋር ሲስማማ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሊባርከው የሚችለው ትዳር ይህ ነው!
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ የትዳር አጋሬን እወዳለሁ ነገር ግን ለሁለት መገመድ በቂ አይደለም፡፡ አንዳችን ለአንዳችን ያለንን ፍቅር አጠንክረህ ለእኛ ወዳለህ እቅድ እንድትመራን ወደ ትዳራችን አንተን በመጋበዝ ድርሻዬን መወጣት አፈልጋለሁ፡፡