ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው? – ማቴ 6:27
ጭንቀት ምንም ጥሩ ነገር የለውም፤ አንድም ነገር አይቀይርም እናም እኛ ምን ማድረግ ለማንችላቸዉና እግዚአብሔር ብቻ ለሚችላቸዉ ነገሮች ስንጨነቅ ጊዜአችንን እናባክናለን፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ተጨንቀን በቁመታችን ላይ አንዲት ስንዝር እንኳ መጨመር እንደማነችል ይነግረናል፡፡ ነገር ግን ብንጨነቅ አሁንም ብንጨነቅ ጭንቀት የትም ሊያደርሰን አይችል፡፡
በተበሳጨን ቁጥር ስሜታዊ ሐይላችንን እናጣለን፣ ጤናችን ይዛባል፣ ሰላማችን ይወሰዳል ግን ጭንቀት አንዲት ነገር አይለዉጥልንም፡፡ እኛ መፍታት የማንችላቸዉንና እግዚአብሔር ብቻ የሚችላቸዉን ነገሮች ለመፍታት መጣር አይጠበቅብንም፤ በዚህ ምክንያት እያጨበጨበ የሚስቅብን ዲያብሎስ ብቻ ነዉ፤ በደጋሚ አገኝኋቸው እያለ።
ኢዩሱስ በዮሐ 14፡27 ልባችሁ አይታወክ በዮሐ 13፡33 ደግሞ አይዞአችሁ ይለናል፡፡ ይህ ስናደርግ ለሰይጣን ክፉ ምት እንደሚሆን አስባለሁ፡፡ ሁሉንም ነገር መፍታት እንደማትችሉ ስታዉቁ ታርፋላችሁ ትረጋጋለችሁ ደግሞም እግዚአብሔር ሁሉ እንደሚችል ስታዉቁ በደስታ ትሞላላችሁ
ስለዚህ ከመጨነቅ ይልቅ ተረጋጉ እና ተደሰቱ ይህ ዲያብሎስን ከእናንተ ያርቃል፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ! ጭንቀቴ ምንም አለመጣልኝም ስለዚህ እተወዋለሁ፤ እኔ መፍታት የማልችለዉን ነገር ስለምትፈታ አመሰግንሃለሁ፡፡ አሳርፈኝ በደስታም ሙላኝ፡፡