በተስፋ መጠባበቅ

በተስፋ መጠባበቅ

ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። – ማቴ 7፡7

በሕይወትህ ስላለ ጉዳይ እየጸለይክ እንዳለ ለውጥ ለማየት ስትጠባበቅ ራስህን አግኝተኸው ታውቃለህ? መልሱ እስከአሁን ያልመጣዉ ለምንድነዉ እያልክ ይሆን? ድል አልፎህ እንደሄደ ይሰማሃል?

አንዳንድ ጊዜ በይህወታችን ስላለዉ ሁኔታ ረጅምና ከባድ ጸሎት አድርገን መልሱን ሳንቀበል ስንቀር ከሁኔታዉ ጋር መኖርን እንማራለን፡፡ እግዚአብሔር ይመልስልን ይሆን እያልን ወደ ሥራችን እንሄዳለን፡፡ ነገር ግን እኛ በዝርዝር ባናዉቀዉም እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቶ መልሱን እየሰራልን ነዉ፡፡ ሁኔታዎቻችን በድንገት፣ በፍጥነት ያለማስጠንቀቂያ ሊለወጡ ይችላሉ፡፡

እስከዚያዉ ድረስ ግን በተስፋም ይሁን በቸልታ ልንጠብቅ እንችላለን፡፡ ንቁ ያልሆነ ሰዉ ተስፋ ይቆርጣል፤ በሌላ በኩል የሚጠባበቅ ሰዉ ግን በተስፋ የተሞላ፣ መልሱ እንደተቃረበ ፣ በማንኛዉም ደቂቃ ሊያገኝ እንደሚችል የሚያምን ነዉ፡፡ ልቡ በተስፋ የተሞላ ነው፡፡ በየቀኑ የሚነቃዉ መልስ እንደሚያገኝ እየተጠባበቀ ነዉ፡፡ ሊጠብቅ ይችል ይሆናል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በድንገት በዙሪያዉ ያለዉን ነገር እስኪለዉጥ መጠየቁን የሚቀጥል ነዉ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! በዝለት ሳይሆን በንቃት ልጠባባቅ እፈልጋለሁ፡፡ አንተ በትክክለኛዉ ሰዓት እንደምትመልስ በማወቅ ጥሶ መዉጣትን እንድትሰጠኝ እጠይቅሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon