በታደሰ ሕይወት ኑር

በታደሰ ሕይወት ኑር

እንግዲህ ከጌታ ፊታ የመጽናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድላክላችሁ ኃጥያአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ፡፡ ዮሐ. ሥራ 3 19

እግዚአብሔር መኖሩን በብዙ መንገድ ይገልፃል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ባናየውም ነገር ግን እንደ ንፋስ በእኛ ውስጥ የሚሠራውን እናያለን፡፡ ሲደክመኝ፣ ስዝል፣ ተስፋ ስቆርጥ፣ በሆነ ጉዳይ ተቸግሬ ሳለሁ ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ ወስጄ በፊቱ ስቆይ በሕይወቴ እታደሳለሁ፡፡ ይህም የእግዚአብሔር መንፈስ ንፋስ በሕይወቴ እንደነፈሰ አውቃለሁ፡፡

እግዚአብሔር በህይወትህ ብርታትን ሊያመጣ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በነፍስህ ተስፋ አትቁረጥ ወይም በትንሹ ተስፋ ቆርጠህ አትቁም መልሱ በውስጥህ እያለ ከእግዚአብሔር ጋር ለመውሰድ ባይመችሁ ዝም ብለህ እየባከንክ ነህ፡፡ ስለዚህ በጊዜ አጠቃቀምህ ላይ የተወሰነ ማስተካከያ አድርግ፡፡ በሕይወትህ ተመልሶ ብርታትን የማግኘት እድል እያለህ መጥፋት፣ በቀላሉ መሸነፍ፣ መዛልና መድከም የለብህም፡፡ ኢየሱስ እንዳደረገው ከውጥረት ሕይወት ወጥተህ ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ የማሳለፍ ሕይወት ተማር፡፡ በዙሪያ ያሉ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ልታሳልፍ የሚገባህን ጊዜ እንዲወስኑልህ ልትጠብቅ አይገባህም፡፡ የሆኑ ሰዎች ምናልባት አንተ ሁልጊዜ የሆነ ነገር እንድታደርግላቸው ያስቡ ወይም ይፈልጉ ይሆናል፡፡ በማለዳ በመጀመሪያ ጊዜህን ከፋፍለህ ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ ጥቃቅን መንፈሳዊ የመዝናኛ ጊዜያቶች በቀን ውስጥ ይኑርህ፡፡ እየሠራ ያለውን ሥራ ለሁለትና ለሦስት ደቂቃዎች በማቆም እረፍት እንዲሰማ በረጅሞ እየተነፈስክ ለእግዚብሔር ምን ያህል እንደምትፈልገውና እንደምትወደው በቀላሉ ንገረው፡፡ ከዚያ በእርሱ መገኘት ውስጥ ሆነ በቀረው ደቂቃዎች በእርሱ ሬት ፀጥ በል በሕይወትህ የሚገርም ሁኔታ ስትታደስ ታያለህ፡፡

ዛሬ ለእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- በጌታ መገኘት ውስጥ በመሆን እራስህን አድስ እንጂ በድካምና በመዛል አትጥፋ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon