
በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚ ጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሿሿ ጸናጽል ነኝ። – 1 ኛቆሮ 13፡1
በትዳራችን የመጀመሪያዎቹ ወቅቶች ላይ እግዚብሔር ካስተማረኝ ነገሮች መካከል ዳዊትን በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ መውደድ ትዳሬን መሰዋት ማድረግ መሆኑን ተምሪያለሁ፡፡እስኪያዘው ዕለት ድረስ ግን ልክ እንደሚንሸዋሸዉት ፅናፅሎች አይነት እራሴን በሚያስደስቱኝ ነገሮች ዙሪያ ብቻ ነበርኩ፡፡
ፍቅር የዕድገትና የብስለት ደረጃችንን ማሳያ ነው፡፡ በመሰዋዕት የሆነ ስጦታንም ሁልጊዜ ይሻል፡፡ምናልባት ሌላኛውን ሰው ፈፅመን አንወደውም ይሆናል ዋጋ እየከፈልን ካልሆነ እያደረገን ያለው እያስመሰልን ነው ማለት ነው፡፡
መረዳት ያለብን ነገር እውነተኛ ፍቅር እራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ነው፡፡ ስለዚህ ውሳኔያችሁ ሁልጊዜም አብሯችሁ ያለውን የትዳር አጋራችሁን ሊያስደስት ይገባል። ይህንን ስታደርጉ እያደረጋችሁ ያላችሁት እራሳችሁን እየሰጣችሁ ነው፡፡
ለባልና ለሚስት የእግዚያብሔር ዓላማ እርስ በእርስ ያለምንም ቅድመሁኔታ እንዲዋደዱ ነው፡፡ ይህ ማለት ነገሮች ሁልግዜም በአንተ መንገድ ላይሄዱ ይችላሉ ማለት ነው፡፡ መለካሙ ዜና ግን ባልና ሚስት ራስወዳድነትን አሳልፈው ሲሰጡ አሸናፊ ትዳር ይኖራቸዋል!
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚያብሔር ሆይ በትዳሬ ውስጥ በእውነተኛ ፍቀር መመላለስ እፈልጋለሁ ፤ በራሴ መንገድ መሄዴን ትቼ ለትዳር አጋሬ ዋጋ መክፈል መጀመርን ዛሬ ወስኛለሁ፡፡