በንጽጽር ምንም አይደለም

በንጽጽር ምንም አይደለም

የአሁኑ ዘመን (ይህ የአሁኑ ህይወት) ሥቃያችን ወደ ፊት ሊገለጥ ካለው ለእኛ ከተጠበቀልን ክብር ጋር ሲነጻጸር ምንም እንዳይደለ እቈጥራለሁ። ሮሜ 8፥18

የክርስቶስን መከራ መካፈል ማለት ምን ማለት ነው? ዋናው ነገር በማንኛውም ጊዜ ሥጋችን አንድ ነገር ማድረግ ሲፈልግ እና የእግዚአብሔር መንፈስ ደግሞ ሌላ ነገር እንድናደርግ ሲፈልግ እኛ መንፈስ ቅዱስን ለመከተል የመረጥን እንደሆነ ሥጋችን ይታመማል። እኛ ያንን አንወደውም፣ ነገር ግን የዛሬው ጥቅሳችን የክርስቶስን ክብር ለመካፈል ከፈለግን የእርሱን መከራም ለመካፈል ፈቃደኞች መሆን እንዳለብን ይናገራል። የእግዚአብሔርን መንፈስ በመታዘዝ ውስጥ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት የነበረብኝን መከራ አሁንም ድረስ አስታውሳለሁ። እንዲህም አስቤ ነበር። ‘ውድ እግዚአብሔር፣ ከዚህ እገላገል ይሆን ? ꞌ መቼም አንድ ቀን ያለህመም አንተን መታዘዝ የምችልበት ደረጃ ላይ እደርስ ይሆንን?

አንዴ ከሥጋ ፍላጎት ቁጥጥር ውጭ ከሆንን፣ እግዚአብሔርን መታዘዝ ቀላል ወደሚሆንበት ደረጃ ላይ እንደርሳለን፤ በእርግጥ እርሱን በመታዘዝ ደስ ወደምንሰኝበት ደረጃ ላይ እንደርሳለን። በአንድ ወቅትለማድረግ በጣም ከባድ እና ፈታኝ የነበሩ ነገር ግን አሁን ለእኔ ለማድረግ ቀላል የሆኑ ነገሮች አሉ፣ እናም በአስቸጋሪ ሁኔታዎች አልፎ ወደ ክብሩ ለመድረስ ፈቃደኛ ለሆነ ሁሉ ተመሳሳይ ነገር ይከሰታል።

በሮሜ 8፡ 18 ውስጥ ጳውሎስ በመሠረቱ እንዲህ ብሏል፣ “አሁን ትንሽ መከራን እንቀበላለን፤ እና ምን ይሁን? ከመታዘዛችን የተነሳ ሚመጣው ክብር አሁን ከምንጸናበት መከራ አብዝቶ ይበልጣል” ያ መልካም ዜና ነው! የምንቀበለው መከራ ምንም ይሁን ምን፣ በምንም ውስጥ ብናልፍ፣ በሕይወታችን ውስጥ ከእሱ ጋር መጓዛችንን ስንቀጥል እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ ሊያደርጋቸው ካሉ መልካም ነገሮች ጋር ሲወዳደር በፍጹም ምንም አይደለም።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ከእሱ ጋር ወደፊት ለመጓዝ ስትቀጥል እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ታላላቅ ነገሮችን ያደርጋል።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon