
ሰላሜን እተውላችኋለሁ፤ሰላሜን እሰጣችኋለሁ… – ዮሐ 14፡27
ኢየሱስ ይህንን ምድር ለቆ ሲሄድ ሰላሙን ከእኛ ጋር ትቼዋለሁ ብሏል፡፡አሁን ልንወስን የሚገባው ውሳኔ እርሱ በሰጠን ሰላም ለመኖር እንመርጣለን ወይ?የሚለው ነው፡፡
አውነት ነው ሰይጣን እናንተን ለማናደድ ያለማቋረጥ ይሞክራል፡፡ለምን?ምክንያቱም ሰላማዊ ካልሆናችሁ እግዚአብሔርን መስማት እንደማትችሉ ያውቃል፡፡
ሰላማችሁን ለመስረቅ ብቻ ሰይጣን በሳምንት ስንት ጊዜ ጥቃትን እንደሚሰነዝርባችሁ ህይወታችሁን ብትመለከቱት ትደነቃላችሁ፡፡ለመጨረሻ ጊዜ ያንን ሳይ ጌታ በመንፈሴ፣ጆይስ ሰይጣን ሰላምሽን ያንን ያህል ከፈለገው ሰላማዊ መሆን ውስጡ የሆነ በጣም ሀይለኛ ነገር አለ ማለት ነው አለኝ፡፡
እውነት ነው!ስለዚህ አሁን ሰይጣን ሰላሜን ለመስረቅ ሲሞክር ከእርሱ እየበለጥኩ እንደሆነ በማወቅ አጥብቄ መያዝ ያዝናናኛል፡፡ያ ማለት አልከፋም ማለት አይደለም ነገር ግን የሆነ አዎንታዊ ነገር አደርጋለሁ ራሴን ተቆጣጥሬ ለሆነ አላማ ስል ሰላማዊ እሆናለሁ፡፡
በአላማ ሰላማዊ መሆን ለራሳችን ብለን ልናደርገው የሚገባ ነገር ነው፡፡የእግዚአብሔርን ሰላም ትመርጣላችሁ?
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ ሰላምህን ስለሰጠኸኝ አመሰግንሀለሁ፡፡ሰይጣን ሰላሜን ለመስረቅ ሲሞክር፣አላማውን ግለጥልኝ፡፡ሰላሜን እንዲወስድ አልፈቅድለትም፣ይልቁንስ ከአንተ ስሬን ተክዬ እቀራለሁ፡፡