በአንድ ጊዜ አንድ ጉዳይ በአንድ ቀን

በአንድ ጊዜ አንድ ጉዳይ በአንድ ቀን

በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋ ነውና ጽና ፣ አይዞህ አትፍራ ፣ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁምን .. – ኢያሱ 1፡9

በአንድ ጊዜ አንድ ተግዳሮት ብቻ እንድትጋፈጡ አጠንክሬ እምክራችኋለሁ፡፡ በመንገዳችን ርቀት ላይ ብዙ አርቆ ማየት ሊያጨናንቀን ይችላል፡፡ እግዚአብሔርን ማመን የዕለት እንጀራችንን እንደሚሰጠን ማመንን ይጨምራል ፤ የሚያስፈልገንን ነገር በሚያስፈልገን ጊዜ እናገኛለን ፤ ግን ከሚያስፈልገን በፊት አናገኘውም፡፡

አንዳድ ተግዳሮቶች የማይቻሉና የሚያጨናንቁ ይመስላሉ ፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ዘወትር ከእኛ ጋር ነው፡፡ የሚሰጠንን ብርታት ከእርሱ በመቀበል መበርታት ይገባናል፡፡

አስታውሱ ዛሬ ማድረግ የሚገባችሁን እንድታደርጉ ጸጋውን ይሰጣል ፤ ትኩረት ማድግ ያለብንም አሁን ምን ማድረግ እንዳለብን እንጂ ስለ ነገ መጨነቅ አይደለም፡፡

ይህ መርህ ለበርካት የሕይወታችንን አቅጣጫ ይረዳናል – ከእዳ ለመውጣት ፣ ቤት ለማጽዳት እና ለማሳናዳት ፣ በትዳር ውስጥ የሚገጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ፣ ልጅን ለመቅጣት ፣ በስራ ገበታ ላይ በሰዓቱ ለመገኘት ወይም ስራን በወቅቱ ለመጨረስ ሁሉ ይረዳናል፡፡ ማድረግ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

ፊሊጲሲዩስ 4፡13 ለማንኛውም ነገር ዝግጁ ናችሁ፣ እና ክማንኛውም ጋር እኩል ናችሁ ምክንያቱም እግዚአብሔር ብርታትን ሰጥቷችኋል፡፡ እርሱ በእናንተ ውስጥ ከሆነ ትልቅ የሚባል ነገር የለም፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በፊቴ ያለው ተግዳሮት የማይቻል ሲመስል ተራ በተራ እንደማሸንፈው አውቃለሁ ምክንያቱም አንተ ከእኔ ጋር ነህ፡፡ ብርታትህን ዛሬ ከአን እቀበላለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon