በኢየሱስ ያለን ድል

በኢየሱስ ያለን ድል

ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ፥ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የክብርና የምስጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን። – ዕብ 2:9

መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ሞትን የቀመሰዉ ለእኛ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ስለዚህ እርሱ ሞታችንን ሞቶ እዳችንን ስለከፈለና የዘላለም ህይወት ስለሰጠን የዘላለም ሞት አንቀምስም፡፡ ይህ አንዱ የምትደሰትበት ነገር ነዉ፡፡

በኢየሱስ ትንሳኤ ሞት ድል ስለተነሳ በእያንዳንዱ ማለዳ በኢየሱስ ያገኘነዉን ድል ለመኖር የመጠቀም ዕድል አለን፡፡ ክርስቲያኖች በማለዳ ወለሉ ላይ እግራቸዉን ሲያደርጉ ሲኦል እንደሚንቀጠቀጥ አምናለሁ፤ እኛ መንቃታችንን ሲያስተዉሉ አጋንንት ይንቀጠቀጣሉ፡፡

ይሄ የሚሆነዉ ማን መሆናችንንና በክርስቶስ ያለንን ስልጣን መረዳት ስንጀምር ነዉ፡፡ እኛ በእግዚአብሔር ሰራዊት ዉስጥ ወታደሮች ነን፡፡ በእርሱ ስልጣን አለን፡፡

ኢየሱስ ሞትንና ኀጢአትን ድል ነስቷል፡፡ አሁን እርሱ በሰጠን ስልጣንና ድል ልንመላለስ ያስፈልጋል፡፡ ይሄኔ ነዉ ለእግዚአብሔር ጠላቶች እጅግ አደገኛ የምንሆነዉ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በአንተ ስላለኝ ስልጣን አመሰግንሃለሁ፡፡ አንተ በሰጠሀኝ ስልጣን እንድመላለስና የከፈልክልኝን ዋጋ የበለጠ በመረዳት እለት እለት በሰጠሀኝ ስልጣን እንድመላለስ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon