በእርሱ ላይ ተደገፍ

በእርሱ ላይ ተደገፍ

. . . ስለ እምነታችሁ ለቅዱሳንም ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ሰምተን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔር ሁልጊዜ እናመሰግናለን፡፡ ቆላ 1፡4

እግዚአብሔር ከማንኛውም ነገር ሁሉ በላይ ሙሉ በሙሉ በእርሱ ላይ እንድንደገፍና እርሱን በመስማት እንድንታዘዘው ይፈልጋል፡፡ እምነት ማለት እንግዲህ ያ ነው፡፡ በዛሬው ጥቅሳችን ውስጥ ለእምነት የተሰጠው ትርጉምና በእያንዳንዱ ጉዳያችን ላይ በጌታ የመደገፋችንን እውነታ እወዳለው፡፡

እግዚአብሔር በራሱ ፈቃድ ውስጥ እንዲጠብቀን እንደገፈዋለን፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ያስደስታል፡፡ ምክንያቱም በራስ ጥረት በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ለመቆየት በጣም ያስቸግራል፡፡ በሕይወትህ እኔ መቶ በመቶ በየቀኑ የማደርገውን አውቃለው የምል ወይም የምትል በእርግጠኝነት ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ ትክክለኛ ውሳኔ ለማድረግ ሁሉንም ነገር ማድረግ እንዳለብን እናውቃለን፡፡ ትክክለኛ መሆናችንን በምን እናውቃለን; አንችልም፡፡ እግዚአብሔር በፈቃዱ ውስጥ እንዲጠብቀን እርሱ መታመን አለብን ጠማማ መንገዳችንን ከፊታችን እንዲያቀነልንና በጠባቡ የሕይወት መንገድ ላይ እንዲመራን ከሰፊውና ወደ ጥፋት ከምወስደው መንገድ እንዲጠብቀን መፀለይ አለብን፡፡ (የማቴ 7 13)

‹‹እግዚአብሔር ሆይ በሕይወቴ ፈቃድህ ይሁን!›› ብለን መፀለይ ያስፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር ለሕይወቴ ያለውን ፈቃዱን በጥቂቱ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱን ነገር አላውቅም፡፡ ስለዚህ ደግሞ በማረፍና በፀጥታ በተረጋጋ ሠላም ውስጥ ሆኜ በመማር በእግዚአብሔር ላይ መደገፍ እራሴን ለእርሱ በመስጠት ፈቃዱ በእኔና በሕይወቴ እንዲሆን መፀለይ አለብኝ፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሰነፍና ደካማ ሰዎች ብቻ በእግዚአብሔር ላይ የምደገፉ መስሎን እንደዚያ እናስብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በእግዝአብሔር ላይ መደገፍ በጣም ጥሩ ነገር እንደሆነ ታምራለሁ፡፡

ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ዛሬ ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ላይ ተደገፉ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon