በእሳቱ ውስጥ

በእሳቱ ውስጥ

« … አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና» (ዕብ. 12፡29)።

እግዚብሔር በህይወታችን ውስጥ ማንኛውንም ለእርሱ ክብር የማያመጣውን ነገር ሁሉ ሊያጠፋውወይም በእሳቱ ሊያቃጥለው ይፈልጋል። እርሱ ከእኛ ጋር የጠበቀ ህብረት ይኖረው ዘንድ፣ ማንኛውንም የተሳሳተ አስተሳሰባችንን፣ ንግግራችንን ወይም ድርጊታችንን ሊያርምን ውም ሊወቅሰን መንፈስ ቅዱስ በእኛ በአማኞች ውስጥ እንዲኖር ልኮታል። ሁላችንም
«በሚያጠራ እሳት» ውስጥ እናልፋለን።

«የሚያጠራ እሳት» ምን ማለት ነው? የእግዚአብሔር ፈቃድ ከእኛ ጋር ይሠራል ማለት ነው። እርሱ የእኛን አመለካከቶችን፣ ፍላጎቶችን፣ መንገዶችን፣ ሀሳቦችንና ንግግሮችን ሊለውጥ ይሠራል። እርሱን የማያስደስተውን በልባችን ውስጥ ስላለው ነገር ይነግረናል። እንዲሁም እነዛን ነገሮች በእርሱ እርዳታ ከእኛ እንዲለወጡ ይጠይቀናል። እኛ በሚያጠራው እሳት ውስጥ ማለፍን ትተን ከእርሱ ከመሸሽ ይልቅ በእርሱ ውስጥ የምናልፍ ከሆነ በመጨረሻ ለእግዚአብሔር ትልቅ ክብር የምናመጣ እንሆናለን።

በእሳት ውስጥ ማለፍ በእውነት አስፈሪ ነገር ነው። በህመም፣ በሞት ጭምር ውስጥ ማለፍ አስፈሪ እንደሆነ ያስታውሰናል። በሮሜ 8፡17 ጳውሎስ ሲናገር የክርስቶስ ወራሾች መሆን የምንፈልግ ከሆነ የእርሱንም መከራ መካፈል አለብን። የኢየሱስ መከራ እንዴት ነበር? ወደ መስቀል መሄድን እንጠብቅ ይሆን? መልሱ ነውም ወይም አይደለምም ነው። ለኃጢአታችን በስጋ በመስቀል ል በሚስማር መቸንከር አያስፈልገንም። ነገር ግን በማር.8፡32 መሠረት ኢየሱስ እንደተናገረው እኛ መስቀላችንን ተሸክመን እርሱን መከተል እንደሚጠበቅብን ተናግሯል። እርሱ ሊናገር የፈለገው እኛን የራስ ወዳድነት ራስ ተኮር የሆነ የህይወት ሥርዓት ማስወገድ እንዳለብን።

መጽሐፍ ቅዱስ እኛ ለእኔነት /ለራስ/ መሞት እንዳለብን ይናገራል። እመነኝ ራስ ወዳድነትን ማስወገድ ጥቂትም ቢሆን እሳት ይጠይቃል። እንዲያው በተለምዶ ብዙ እሳትም ይጠይቃል። ነገር ግን በእሳት ውስጥ ለማለፍ ፈቃደኛ ከሆንን በኋላ ል እኛ በእግዚአብሔር ክብር ደስታ እንደምናገኝ እናውቃለን።


ዛሬለአንተያለውየእግዚአብሔርቃል፡ እግዚአብሔር እጅግ በጣም ይወደናል፣ እንዲሁም እርሱ በቀጣይነት ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ በእኛ ውስት እየሠራ ነው።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon