በእግዚአብሔር ህልውና ደስ ይበልህ (ሐሴትን አድርግ)

በእግዚአብሔር ህልውና ደስ ይበልህ (ሐሴትን አድርግ)

«…የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ» (መዝ.16፡11)።

እኔ በግምባሬ ወደ መሬት ተደፍቼ መጸለይን ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርንና ከእርሱም ድምጹን መስማትን እወዳለሁ። ይህ ዓይነት በአካል መሬት ል መደፋት ሌሎች ሁሉንም ነገሮች ዘግቼ ከእግዚአብሔር ጋር ለብቻ መሆን የሚል ስሜት ይሰማኛል።ወገቤ ላይ ህመም እስከሚሰማኝና እስካቆመው ድረስ በዚህ ዓይነት መንገድእጸልያለሁ።የጸሎት የሰውነት አቀራረቤን ስቀይር መንፈሳዊነት የጎደለው ሆንኩ የሚል ስሜት ውስጥ ስለማልገባ ደስተኛ ነኝ።የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት ወይም፣ የእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ ለመኖር ወይም፣ ለመጸለይ ብለን አንድ የተወሰነና ሁልጊዜ የማይለወጥ በጥንቃቄ ልትጠብቀው የምትታገለው በአካል የሚገለጥ የጸሎት አቀራረብ ልነግርህ እችላለሁ። ጉልበት ህመም ከተሰማው፣ መሬት ላይ ተኛ። ወገብህ ህመም ከተሰማው ወርት ላይ በመተኛት፣ በመነሳትና በዙሪያው መንቀሳቀስ ይቻላል። እንደ ባለቤቴ ዴቭ መሆን የምትፈልግ ከሆነ አንተም ቁጭ ብለህና በመስኮት ወደ ኋላ በመመልከት፣ ከዚያም ወንበር በመሳብና በመቀመጥ መጸለይ ትችላለህ። ከእግዚአብሔር ጋር የምትነጋገርበትንና ከእርሱ የምትሰማበትን ለአንተም ምቾት የሚሰጥህና በእርሱ ላይ ትኩረት የምታደርግበትን ቦታ ፈልግ።

ይህ ነው ተብሎ ከሰማኸው ማንኛውም ዓይነት የጸሎት ቀመርና ከሚያቀመጥልህ የተቀረጸ የጸሎት አቀራረብ ነጻ ሁንና ጸሎትህ ቀጥል። ከእግዚአብሔር ጋር ያለህን ግንኙነት በጣም ቀለል ያለ ለማድረግ እንድትችል አነግርሃለሁ። ለአንተ በሚመችህና ቀላል በሆነ ከሁሉም በላይ በእግዚአብሔር ህልውና ሊያስደስትህ በሚያስችልህ መንገድ ከእርሱ ጋር ተነጋገርና እርሱን ስማው።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ ጸልይ!

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon