በእግዚአብሔር መደገፍ

በእግዚአብሔር መደገፍ

…እንግዲህ በመንፈስ ኑሩ፤የስጋንም ምኞት አትፈጽሙም… – ገላ 5፡16

ስፋ በቆረጥን ቁጥር በእግዚአብሔር ላይ መደገፋችንን አቁመናል ብዬ አምናለሁ፡፡ይሄ አባባል የድፍረት አባባል ሊመስላችሁ ይችላል፣እስቲ ግን አስቡበት፤እግዚአብሔር በመንገዳችን የሚመጣውን ማንኛውንም ነገር ለማለፍ የሚረዳንን መንፈስ ቅዱስን እና ጸጋውን ለእኔ እና ለእናንተ ሰጥቶናል፡፡በእርሱ ላይ መደገፋችንን ስናቆም እና በራሳችን መንገድ አንድ ነገር ለማድረግ ስንጥር ተስፋ መቁረጥ እንጀምራለን፡፡

ይሄንን መረዳቴ የእውነት እረድቶኛል፡፡ተስፋ በቆረጥኩ ቁጥር እያደረግኩ ያለሁት ነገር የመንፈስ ቅዱስን ቦታ መተካት እንደሆነ እራሴን አስታውሰዋለሁ፡፡ትንሹ መንፈስ ቅዱስ ለመሆን እየሞከርኩ ነበር!

በራስ በሚመራ መንፈስ ተቸግረዋል? በእግዚአብሔር ላይ መደገፍን እምቢ ስትሉ እያላችሁ ያላችሁት “እሺ እግዚአብሔር በዙሪያዬ መኖርህን እወደዋለሁ ነገር ግን ይሄንን ነገር ሳደርግ ተከታተለኝ” ነው፡፡ ምናልባት ስለሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ላይ መደገፍ ከባድ ሊሆን ይችላል፣ነገር ግን በእያንዳንዱ ቀናችን ለምንፈልገው ድል ቁልፍ ነገር ነው፡፡

እግዚአብሔር ሲያድነን ረድቶን ከዛ “በቃ ጨርሻለሁ፡፡ከዚህ በኋላ በራሳችሁ ነው የምትቀጥሉት!” አላለንም፡፡ ያዳነን ለዘላለም ነው፣ይሄም ማለት በእርሱ ከተደገፍን ይመራናል፤ይረዳናል ማለት ነው፡፡

ገላቲያ 5፡16 በመንፈስ እንድንመላለስ እና እንድንኖር የስጋንም ምኞት እንደማንፈጽም ያዘናል፡፡ “ስጋን በግላችሁ አሸንፉት… ከዛም ምኞቱን አትፈጽሙም” አለማለቱን አስተውሉ፡፡ያለው በመንፈስ ኑሩ ነው፡፡

በግላችሁ መኖርን ለማቆም ምረጡ እናም በምትኩ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ተደገፉ፡፡እንደማትጸጸቱ ቃል እገባላችኋለሁ!


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ የምታስፈልገኝ አንተ ብቻ ነህ፡፡በራሴ እንዳልታመን ይልቁንስ በአንተ እንድታመን እና እንድደገፍ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon