በእግዚአብሔር ፈቃድ ደስ ይበልህ

በእግዚአብሔር ፈቃድ ደስ ይበልህ

‹‹ … አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው›› (መዝ.40፡8)።

የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት የምንፈልግ ከሆነ ለፈቃዱ መታዘዝ አለብን፡፡ በየማለዳው ላይ ያሉት ጸሎቶቻችን እንደዚህ እንደሚሆን አምናለሁ፡፡

‹‹ እግዚአብሔር በሁሉም የህይወቴ ክፍል በፍጹሙ ፈቃድህ ውስት መመላለስ እፈልጋለሁ፡፡ እኔ የአንተን የይሁንታ ፈቃድ አልፈልግም፡፡ ያለአንተ ማረጋገጫና በረከቶች እኔ ምንም ነገር ማድረግ አልፈልግም፡፡ አንድ አንተ ከሁሉ የላቀ ለእኔ ያዘጋጀኸው ነገር ካልሆነ ለማድረግ በምሞክርበት ጊዜ እባክህን በልቤ ውስጥ የማወላወል ስሜት ስጠኝ፤ በአንተ እቅድ መንገድ ራሴን እንድጠብቅ ልቤን መርምር፤

ራሴን ላንተ እንዳስገዛ እርዳኝ፤
አንገተ ደንዳና እንዳልሆን እርዳኝ፤
ግትር እንዳልሆን እርዳኝ፤
ልበ ደንደዳና እንዳልሆን እርዳኝ፤

እግዚአብሔር ሆይ የአንተ ፈቃድ በህይወቴ ውስጥ በሙላት እንዲሠራ እፈልጋለሁ፡፡ በእኔ በራሴ ፈቃድ ስጓዝ የማገኘውን ውጤት ምን እንደሆነ በቂ የሆነ ልምድ አለኝና፤ እርሱ ግን አንተ የምትፈልገው ነገር አይደለም፡፡ እርሱም ወደ ክፋት ሁሁ የሚመራኝ ነውና፡፡ ነገር ግን ለአንተ ለመታዘዝ ፈቃደኛ ነኝ፤ ነገር ግን እባክህ አንተ እንዳደርግ እየተናገርከኝ ያለውን ነገር በትክክል ለመስማት እንድችል እርዳኝ አሜን››


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ በእያንዳንዱ ቀን ብዙ ጊዜያት ለእግዚአብሔር እያንሸኳሾክህ ‹‹ ፈቃድህ ይፈጸም›› በል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon