በእግዚአብሔር ፈጽሞ መሞላት

በእግዚአብሔር ፈጽሞ መሞላት

የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይፀና ዘንድ…. እስከ እግዚአብሔም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ…. ኤፌ 3÷17፡19

በእግዚአብሔር መገኘትና ኃይል በየቀኑ መሞላት የሚያስደንቅና በዛሬው ጥቅስ መሠረት ይህ እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፈቃድ ነው፡፡ በራስ ነገር ከመሞላት በእግዚአብሔር መሞላት እጅግ ይበልጣል፡፡ ግለኝነት ለሕይወት አሰቃቂ መንገድ ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ለእርሱና ለሌሎች የምንኖርበት መንገድ ሰጠን፡፡

መጽሐፍ ክርስቶስ ለሁሉ እንደሞተ ያስተምረናል፡፡ ስለዚህ ማንም ከዚህ በኋላ ለራሱና በራሱ የሚኖር የለም፡፡ ነገር ግን ለእርሱና በእርሱ ይኖራሉ፡፡ (2 ቆሮ 5÷15) ኢየሱስ መልካም የሆነ ሕይወት የምንኖርበት መንገድ አበጀልን በደስታና በሠላም የተሞላ ሕይወትን የምንኖርበትን፡፡ ለእራሳችን ደስታና ዓላማ ብቻ ከመኖር ይልቅ ለሌሎች ፍቅር እንድንኖር መንገድ አበጀልን፡፡

በእግዚአብሔር መገኘት ለመሞላት እሱን መፈለግን ይጠይቃል፡፡ የእርሱን ቃል ማጥናትና እርሱ በሕይወታችን መኖሪያ እንዲያደርግ የሚያስችል ባሕሪ ማሳደግን ይጠይቃል፡፡ ቀንህ በመጽፍ ቅዱስ ንባብና ከእግዚአብሔር ጋር ኅርት ማድረግህ ቀንህን በትክክለኛ መንገድ መጀመርህ ነው፡፡ ይህ ቀን ከእግዚአብሔር ለአንተ የተሰጠ ስጦታ ነው፡፡ ስለዚህ አታባክነው፡፡ እርሱ በመገኘቱ ልሞላህ ይጠባበቅሃል፡፡ ስለዚህ ደስታህ ፍጹም እንዲሆን ጠይቀህ ተቀበል፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- በእግዚአብሔር በመሞላት በአንተ በኩል ሌሎችን እንዲደርስ አድርግ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon