በእግዚያብሔር ቃል ውስጥ ኃይል አለ

በእግዚያብሔር ቃል ውስጥ ኃይል አለ

ከዓይንህ አያርቁ ፤ በልብህ መሃል አስቀምጣቸው። ለሚያገኙት ሁሉ ሕይወት ናቸው ፣ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ እና ጤና ናቸው። – ምሳሌ 4፡21-22

መፅሐፍ ቅዱስ ተራ መፅሃፍ አይደለም። በውስጡ በእያንዳንዱ ገጽ የያዛቸው ቃሎች የህይወታችን መድኃኒቶች ናቸው፡፡ ህይወታችሁን የሚቀይር ኃል በውስጡ አለው ምክንያቱም እርሱ ህይወት ሰጪ ነውና!
የእግዚያብሔርን ቃል እውነትነትና ኃይለኛነት በምትረዱበት ጊዜ ህይወታችሁ ይቀየራል። ሰይጣን በናንተ ላይ የሚያመጣውንም ውሸት ማስተዋል ትችላላችሁ፡፡

መፅሃፍ ቅዱስን ማንበብ ጀምራችሁ ምናልባት በአንድ ጊዜ ሁሉም ነገር ባይገባችሁና ድካም ቢሰማችሁ ትዕግስተኞች ሁኑ ምክንያቱም ዋናው ነገር መጀመር መቻላችሁና ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆናችሁ ነው፡፡ መፅሃፍ ቅዱሳችሁን በምታጠኑበት ጊዜ እርግጠኛ መሆን ያለባችሁ ነገር ቢኖር ከምታነቡት ንባብ ውስጥ እየተማራችሁ መሆኑን ነው፡፡

ምሳሌ 4፡20 ልጄ ሆይ፤ የምነግርህን አስተውል፤ቃሌንም በጥንቃቄ አድምጥ። ይላል። ይህ በጣም ወሳኝ ነው ምክንያቱም ማስተዋል ከማንበብ በላይ ነው፡፡ ይህም ማለት ቃሉን በአዕምሯችን ውስጥ በየዕለቱ ማሰላሰልን ይፈልጋል፡፡

ቃሉን በማንበብና በማሰላሰል በምናሳለፍበት ጊዜ በህወታችን ውስጥ በፈውስና በእግዚያብሔር ኃይል የተሞላ ህይወት ይኖረናል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚብሔር ሆይ ህወትን ስለሚቀይረው ቃልህ አመሰግንሃለሁ! ቃልህን በማጠናበት ጊዜ ከዚያ እንድማር የምትፈልገውን ነገር ንገረኝ በህይወቴም የፈውስን ኃይል ሙላብኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon