በክርስቶስ መተማመን

በክርስቶስ መተማመን

እኛ…በእግዚአብሔር መንፈስ የምናመልክ፣በክርስቶስ ኢየሱስ የምንመካ፣በስጋም የማንታመን ነንና፡፡ – ፊሊጲ 3፡3

እውነተኛ መተማመን ከሚሰማን ስሜት ወይም ልናደርግ ከምንችለው እና ከማንችለው ነገር በፍጹም አይመጣም – የሚመጣው በክርስቶስ ማን እንደሆንን መገለጥን ከማግኘት ነው፡፡ እግዚአብሔር የእውነት ምን ያህል እንደሚወደን ስናውቅ እና ካለፉ ህመሞቻችንን የእርሱን ፈውስ ስንቀበል በስጋ ነገሮች ላይ መተማመናችንን ማኖር እንደሚያስፈልገን ከዚያ በኋላ አይሰማንም፡፡

ከአመታት በፊት ከራስ መተማመን እጦት ጋር ስታገል እንደነበር አስታውሳለሁ ምክንያቱም እንደማውቃቸው ብዙ ሌሎች ሰባኪዎች የኮሌጅ ዲግሪ የለኝም፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይግባውና በእርሱ በምንም ላይ ያልተደገፈ ፍቅር ላይ ማተኮር ስጀምር በራስ መተማመኔን ቃሉ ነሽ በሚለኝ ላይ ማድረግን ተማርኩ – በክርስቶስ የእግዚአብሔር ጽድቅ (2ኛ ቆሮ.5፡21ን ይመልከቱ)፡፡

ካለፈው ህይወታችሁ ስለራሳችሁ የሚሰማችሁን ስሜት ካበላሹ ነገሮች ፈውሶ እውነተኛ የመተማመንን ስሜት ኢየሱስ ሊመልስላችሁ ይፈልጋል። ከእናንተ ጋር የተሳሳተውን ማየት ትታችሁ እግዚአብሔር ጋር ልክ የሆነውን ማየት ስትጀምሩ በእርሱ ከመሆን በሚመጣ መተማመን መመላለስ ትጀምራላችሁ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በክርስቶስ ማን እንደሆንኩ እንድረዳ እና ፈውስህን በአዕምሮዬ እና በስሜቴ እንድቀበል እርዳኝ፡፡ መተማመኔን በአንተ ለማድረግ መርጫለሁ!

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon