በክርስቶስ ያለን ህብረት ኃይል

በክርስቶስ ያለን ህብረት ኃይል

እናንት የታወራችሁ መሪዎች፤ ትንኝን አጥርታችሁ ትጥላላችሁ፤ ግመልን ግን ትውጣላችሁ። – ማቲ 23፡24

ምንያህል አማኝና ምንያህል ቤተእምነቶች እንዳለሁ ማሰብ ይከብዳል፡፡ ይሁንና ያለን አንድ መፅሐፍ ቅዱስና አንድ መልእክት ብቻ ነው ያለው፡፡ ነገርግን በዘመናት መካከል በሰዎች ጠባብ አመለካከትና መኮፈስ የተነሳ የተለያዬ ቤተክርስቲያናትን ሲከፍቱ እንመለከታልን፡፡ ከዚያም አልፎ የተለያዬ የአስተምህሮ ትርጓሜዎችን ለመደገፍና ለማበረታታት ሲባል መፅሐፍ ቅዱስ እንኳ የተላያዬ ቅጂዎች እየተባዛ ነው፡፡

ሁላችንም በምንም መልኩ 100 ፐርሰንት ትክክል ልንሆን እንደማንችል እረዳለሁ፡፡ ብዙዎቹ የምንታገልላቸው ነገሮች በጣም አሳዛኝና ትንንሽናቸው፡፡በማቲ23፡24 ላይ ኢየሱስ ለፈሪሳዊያን ከሰናፍጭ ውስጥ አስራት እንደሚያወጡና ደግሞ ግመል እንደሚውጡ ይናገራል፡፡በጣም ጥቃቅን ለሆነ ነገር ምን ያህል እንደሚጨነቁ ና ለሚጠቀመውና ለዋናው ነገር ያላቸውን ምልከታ ነው የሚያሳየው፡፡

ቅድመ ግመታ፤ጥላቻና ክፍፍል በህይወታችን ውስጥ ቦታ ካገኙ ኃይል አይኖረንም፡፡ ትምክህትን ለማሸነፍ የምንችለው በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር በሆነ የመንፈስ አንደነትና ህብረት ብቻ ነው፡፡የክርስቶስ ፍቅር ምንም ሊከፋፍለን ከሚችል የትኛውም ኃይል የሚልቅ ነው፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ በእኔ ውስጥ መከፋፈል፤ትምህክትና ጥላቻ በር ከፋች የሆነ ማንኛውም ኃጢያት ቢኖር አስወግድልኝ በአንተ ፍቅር መራመድ እፈልጋለሁ በመንፈስም አንድነት ከወንድሞች ጋር በህብረት መመላለስ እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon