በዓለም እንጂ የዓለም አትሁን

በዓለም እንጂ የዓለም አትሁን

ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም። እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉም። ዮሐ 17፡15-16

ብዙ ሰዎች ዛሬ ላይ ቋሚ በሆነ ጫና ዉጥረት ዉስጥ ይኖራሉ፡፡ ዉጤቱ ደግሞ ክስረት፣ ጭንቀትና ተስፋ መቁረጥ ይሆናል፡፡ መልካሙ ዜና ግን በዮሐ 17 መሰረት ክርስትቲያን እንደመሆናችን መጠን በዓለም እንኖራለን ከዓለም ግን አይደለንም፡፡ እንደ አለም በመምሰል በዓለም ሥርዓት ዉስጥ አንመላለስም፡፡ የእኛ አስተሳሰብና አቀራረብ በፍጹም የተለየ መሆን አለበት፡፡

ዓለም ለአስቸጋሪ ሁኔታዎች የምትሰጠዉ ምላሽ ብስጭትና ተስፋ መቁረጥ ነዉ ፤ ነገር ግን እኛ ኢየሱስ በዮሐ 14፡27 እንዳለዉ ልባችን እንዲታወክ መፍቀድ የለብንም፡፡ ይህ ጥቅስ የእኛ አስተሳሰብ ከዓለም መለየት እንዳለበት ጠቋሚ ነዉ፡፡

ትክክለኛ የሆነ አመለካከትና አቀራረብ በዙሪያዬ ያለዉን ነገር ፈጽሞ ሲለውጠዉ አሰተዉዬአለሁ፡፡ ትክክለኛ አመለካከት እግዚአብሄር እንዲሰራ በር በመክፈት ይረዳሃል፡፡ ምንም እንኳ በዓለም ብትከበብም ትክክለኛ አመለካከት የሚፈድልህ በዓለም እንድትሆን እንጂ ከዓለም እንድትሆን አይደለም፡፡

አስተዉል እኛ በክርስቶስ ስለሆንን የሚገጥሙንን ተግዳሮቶች በሰከነ መልኩ እና በድፍረት የመግጠም ብቃት ተሰጥቶናል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ምንም እንኳ በዓለም ብሆንም ከዓለም እንዳልሆንኩ ነግረሀኛል፤ እኔ ያንተን አመለካከትና ልብ መርጬአለሁ፡፡ በዚህ ዓለም መሃል እንኳ በአንተ ሰላምና በክርስቶስ ልብ ልመልስ መርጬአለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon