ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር የተነሳ ነው፤ርህራሄው አያልቅምና፡፡ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ታማኝነትህም ብዙ ነው፡፡ – ሰቆ.ኤር 3፡22-23
እያንዳንዱ ቀን ባለፈው ነገራችን ላይ በር ዘግተን አዲስ ጅማሮን የምንለማመድበት አዲስ መልካም አጋጣሚ ነው፡፡ እግዚአብሔር ቀናትን በሀያ አራት ሰአታት የከፋፈለበት እውነታ በቋሚነት እንደ አዲስ መጀመር እንዳለብን ማስረጃ ነው፡፡ ሁል ጊዜም አዲስ ቀን ፣ አዲስ ወር እና አዲስ አመት አለ፡፡ ነገር ግን እኛ እነዚህን አዲስ ጅማሮዎች እንድንጠቀምባቸው ውሳኔን ማሳለፍ አለብን፡፡
ከየጥፋተኝነት ስሜት እና ከፍርድ ጋር ጦርነት ገጥማችኋል? ከአመታት በፊት ወይም ትናንትና ስላደረጋችሁት ነገር መጥፎ ስሜት ይሰማችኋል? ምንም ያህል ጊዜ ይሁነው ያለፈ ነገር ያለፈ ነው ፤ የሆነው ሆኗል አሁን እግዚአብሔር ብቻ ነው ሊፈጽመው የሚችለው፡፡ የናንተ ድርሻ ጥፋታችሁን ማመን ፣ ንስሀ መግባት እና የእግዚአብሔርን ይቅርታ ተቀብሎ መቀጠል ብቻ ነው፡፡
በሰቆቃው ኤርሚያስ ላይ ነቢዩ ኤርሚያስ በየማለዳው አዲስ በሆነው የእግዚአብሔር ምህረት ያበረታታናል፡፡ በየዕለቱ አዲስ ጅማሮን ይሰጣችኋል፡፡ በየእለቱ አዲስ ጅማሮ እንዲኖረን እግዚአብሔር በየዕለቱ አዲስ ምህረት ስለሚልክ በጣም ደስተኛ ነኝ!
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ በየማለዳው ምህረትህ አዲስ ስለሆነ በጣም ደስተኛ ነኝ! ለእኔ ካለህ ከፍቅርህ ፣ ከምህረትህ ፣ ከርህራሄህ እና ከታማኝትህ የተነሳ በየዕለቱ እንዳዲስ መጀመር አችላለሁ፡፡