በጋብቻ ዉስጥ አንዳችሁ አንዳችሁን አገልግሉ

በጋብቻ ዉስጥ አንዳችሁ አንዳችሁን አገልግሉ

ሚስቶች ሆይ፤ በጌታ ዘንድ ተገቢ በመሆኑ ለባሎቻችሁ ታዘዙ፡፡ ባሎች ሆይ ሚስቶቻችሁን ወደዱ፤ መራራም አትሁኑባቸዉ፡፡ – ቆላ 3፡18-19

ዳዊት በጠዋቱ ሰላጣና ፍራፍሬ መመገብ ይወዳል፡፡ እናም አንድ ቀን ጠዋት ለባለቤቴ የፍራፍሬ ቁርስ እንድሰራለት ጌታ አበረታታኝ፡፡

ችግሩ እኔ የፍራፍሬ ቁርስ ልሰራለት አለፈለግሁም ነበር ፤ ለምንድ ነዉ ሁልጊዜ ይህንን የምሰራለት ብዬ አሰብሁ፤ ጌታ ግን ባለቤቴን ማገልገል ማለት እርሱ ማገልገል እንደሆነ በትዕግስት አስረዳኝ፡፡

ባልና ሚስት አንዳቸዉ አንዳቸዉን በማገልገል ፍቅር ቢያሳዩ ኖሮ ስንት ትዳር ከፍቺ በተረፈ ነበር፡፡ በመሰረቱ ኢየሱስ ነጻ አዉጥቶን ሳለ ዛሬ ሁሉም “ነጻ” መሆን የሚፈልግ ይመስላል፡፡ ነገር ግን እርሱ ያንን ነጻነት በራስ ወዳድነት እንድንጠቀመዉ  አላሰበም፤ እርሱ የትዳር አጋሮቻችንን በፍቅር እንድናገለግል ይፈልጋል፡፡

ባለቤቴን ያለጥርጥር እወደዋለሁ፤ እናም አንዳንድ ጊዜ ያ ፍቅር በተሻለ የሚገለጸው በማገልገል ነዉ፡፡ ቃላት ጥሩ ናቸዉ ግን ደግሞ በፍቅር ስትጓዙ መስጠታችሁ በተግባራችሁ ይታያል፡፡

በፍቅራችሁ ተግባር እንድትጨምሩ አነሳሳችኋለሁ፡፡ የትዳር አጋሮቻችሁን እንዴት መጋለገልና መባረክ እንደምትችሉ ጌታ እንዲያሳያችሁ ጠይቁት።


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! በትዳሬ ራስ ወዳድ መሆን አልፈልግም ፤ የትዳር አጋሬን አንተ እንደምትፈልገዉ እንዳገለግል እርዳኝ፤ ከቃላት በለፈ ማፍቀር እንድችል እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon