በጤናማ እና ጤናማ ባልሆነ ሀፍረት መሀከል ያለው ልዩነት

በጤናማ እና ጤናማ ባልሆነ ሀፍረት መሀከል ያለው ልዩነት

ነፍሴን ጠብቃት ታደገኝም፤መጠጊያዬ ነህና አታሳፍረኝ፡፡ – መዝ 25፡20

በየዕለቱ ሁለት አይነት ሀፍረት ያጋጥመናል እናም ልዩነትን ማወቃችን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

ጤናማ እና መደበኛ የሆነ የሀፍረት አይነት አለ፡፡ለምሳሌ የአንድን ሰው ዕቃ ብጥል ወይም ብሰብር በስህተቴ አዝናለሁ፡፡ምነው ግድ የለሽ ወይም የማልጠነቀቅ ባልሆንኩ ብዬ እመኛለሁ ፡፡አዝናለሁ ነገር ግን ይቅርታ ጠይቄ በመቀበል ህይወቴን መቀጠል እችላለሁ፡፡

ጤናማ ሀፍረት ደካማ ፣ገደብ ያለን እና ፍጹም ያልሆንን ሰዎች እንደሆንን ያስታውሰናል፡፡እግዚአብሔር እንደሚያስፈልገን ያስታውሰናል፡፡

ነገር ግን ጤናማው ሀፍረት በዛ መቆም ሲያቅተው ጤናማ ያልሆነ እና መርዛማ ይሆናል፡፡ሰዎች ይቅርታ ሳይጠይቁ ወይም ሳይቀበሉ ሲቀሩ ራሳቸውን መቅጣት ይጀምሩና ማንነታቸውን መጥላት ይጀምራሉ፡፡

ህይወታችሁን በእንደዚህ ያለ ሁኔታ አታሳልፉት፡፡እንደ እግዚአብሔር ልጅ እና ወራሽ ትክክለኛውን ቦታችሁን አስታውሱ(ሮሜ 8፡17ን ይመልከቱ)፡፡ጤናማ ያልሆነ ሀፍረት በክርስቶስ ዘንድ ማን እንደሆናችሁ እንድትረሱ ያደርጋችኋል ጤናማ ሀፍረት ግን ያለ እርሱ ምንም አለመሆናችሁን ያስታውሳችኋል፡፡ዛሬ እግዚአብሔር ልዩነቱን እንዲያስረዳችሁ ጠይቁት፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ጤናማ ያልሆነ ሀፍረት ቀንበር ሆኖብኝ መኖር አልፈልግም፡፡ምን ያህል እንደምትወደኝ እንዳስታውስ እርዳኝ፡፡አንተ ይቅር ስላልከኝ ራሴን መቅጣት የለብኝም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon