ቢሆንስ…?

ቢሆንስ...?

ወንድሞች ሆይ፤ እኔ ገና እንደያዝሁት አድርጌ ራሴን አልቈጥርም፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ ከኋላዬ ያለውን እየረሳሁ ከፊቴ ወዳለው እዘረጋለሁ። አንድ የማደርገው አንድ ነገር ያለፈውን ረሳሁ እና ወደ ፊት ወደፊት መጓዝ ነው ፡፡ – ፊሊጵ 3፡13

ሰዎች ብዙ በኖሩ ቁጥር ከሚያዳብሯቸው ሃሳቦች መካከል ምናልባት የሚለውን ሲሆን በዚህም ምክንያት በፀፀትና በቁጭት በሃሳብ ይብሰለሰላሉ፡፡ይሁንና ለክርስቶስ ተከታዮች ግን የምስራቹ ምናልባት የሚለው ሃሳብ የኋለኛውን ዘመን እያሰቡ በቁጭት የሚያንሰላስሉበትና የሚቆጩበት ሳይሆን እግዚያብሔር ለወደፊቱ ለእነሱ ያቀደውን እያሰቡ ሚደሰቱበት ነው፡፡

በመጋቢያቸው አራት ነገሮችን ለአንድ ወር ያህል በማድረግ ስለሚመጣው ዘመን እንዲያስቡ የተደረጉ ጉባኤያትን አውቃለሁ፡፡ እሱም የጠየቃቸው ጥያቄ በየቀኑ እንዲፀልዬ፤በሳምንት አንድ ጊዜ እንዲፆሙ፤አስራት እንዲያወጡ፤ አንድ ያልዳነ ሰው በእያንዳንዱ ሳምንት ይዘው እንዲመጡ ነው፡፡ውጤቱም በዚህች ቤተክርስቲያን ከተጠበቀው በላይ የሆነ ነገር መከሰት ጀመረ የእግዚያብሔር ህልውና እየጨመረ መምጣት ጀመረ ፣ ለቤተክርስቲያናቸው ግንባታ ለማከናወን የሚያስችል ገንዘብ ምንጭና ድጋፍ ይጎርፍ ጀመረ። በጣም አስገራሚው የቤተክርስቲያኒቱ ምዕምናን ነፍሳት ለክርስቶስ እየማረኩ በማምጣት ህወት ውስጥ ተመሉ፡፡

እኔም እናንተን መፈተን እፈልጋለሁ ፤ ልክ እንደዚያ ቤተክርስቲያን ለምን እግዚያብሔርን አሁን መከተል አትጀምሩም? ህይወታችሁን ለምን ሙሉ በሙሉ አትሰጡትም? ወደፊት ብትሔዱስ? ምን ይከሰት ይሆን?


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ በእህይወቴ ውስጥ ቢሆን ኖሮ እያልኩ መጠየቅ አልፈልግም፤ ከአንተጋር አዲስ ግንኙነት ማድረግና አንተን መከተል እፈልጋለሁ በህይወቴም የምታደርገውን አስደሳች ነገሮችን ለማይት ጓጉቼያለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon