በእርሱና በእርሱ ላይ ባለን እምነት አማካይነት፣ በነጻነትና በልበ ሙሉነት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንችላለን። (ኤፌሶን 3፡12)
በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብ በፍጹም ፍርሃት ሊሰማን አይገባም። እሱ ሁሉንም ድክመቶቻችንን ያውቃል፤ ሆኖም ግን ይወደናል። እግዚአብሔር ከበቂ በላይ ሊሰጠን ይፈልጋል፣ እንዲሁ በቂ የሆነ አይደለም፤ እናም በድፍረት ልንጠይቀው ያስፈልጋል።
በድፍረት ወደ እግዚአብሔር በጸሎት መቅረብ ገንዘብ ለማውጣት ወደ ባንክ ከመሄድ ጋር ሊመሳሰል ይችላል። ባንክ ቤት 50 ብር እንዳለኝ ካወቅኩ ምክንያቱም ባሳለፍነው ሳምንት እዚያ ስላስቀመጥኩኝ ወደ ክፍያ መስኮት ለመሄድ እና ሃምሳ ብር ለመጠየቅ ወደ ኋላ አልልም። ገንዘቡ እንዳለኝ አውቃለሁ፤ የእኔ ገንዘብ ነው፤ እና ከፈለግኩት ከባንኩ ማውጣት እችላለሁ። መጠየቂያዬን ሳቀርብ አምሳ ብሬን አገኛለሁ ብዬ ሙሉ በሙሉ እጠብቃለሁ። በዚያ ዓይነት ድፍረት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ያለብን በራሳችን ጽድቅ የተነሳ ሳይሆን ከኢየሱስ ጋር ወራሾች የመሆን መብት በማግኘታችን ነው። በኢየሱስ ምክንያት ለእኛ ምን እንደሆነልን መገንዘብ ያስፈልገናል እናም የእኛ የሆነውን እናገኛለን ብለን ሙሉ ተስፋ በማድረግ በልበ ሙሉነት መጸለይ ያስፈልገናል።
እግዚአብሔር በክርስቶስ ለእኛ የማይታመን ነገር ሰጥቶናል፤ እናም እሱ ቀድሞውኑ ለእኛ የገዛልንን በረከቶች በኢየሱስ ስም መጠየቅ ብቻ ነው የሚያስፈልገን። ብቁ ያለመሆን ስሜቶች ጋር ስንታገል ወደ እግዚአብሔር ቃል መሄድ እና የእግዚአብሔር ልጆች እንደመሆናችን መጠን ያለንን መብቶች እንዲያስታውሰን እናድርግ። በድፍረት ወደ እግዚአብሔር መገኘት እንድንገባ እና እንድንቀበል መንፈስ ቅዱስን ጠይቀን የሚያስፈልገንን እርዳታ ማግኘት ያስፈልገናል ምክንያቱም “እኛ የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆንን ራሱ መንፈስ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል፣ ልጆችም ከሆንን ደግሞ ወራሾች ማለትም የእግዚአብሔር ወራሾች እና ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን” (ሮሜ 8፡16-17)። እርሱ ይናገረናል ደግሞም የእግዚአብሔር መሆናችንን ያስታውሰናል!
የእግዚአብሔ ቃል ለአንተ ዛሬ: አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እናም መልካም ሊሆንልህ እየፈለገ እና እየጓጓ ነው።