“አቤቱ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ‘እኔ ለአንተ ቤት እሠራልሃለሁ’ ብለህ ይህን ለባሪያህ ገልጸህለታል። ስለዚህ ባሪያህ ይህችን ጸሎት ወደ አንተ ለማቅረብ በልቡ ደፈረ። (2 ሳሙኤል 7:27)
እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ይናገረንና “የጸሎት ተልዕኮ” ይሰጠናል። ንጉሥ ዳዊት የእግዚአብሔርን ቤት የመስራት ተልእኮ ተሰጥቶኛል ብሎ ስላመነ እስኪያልፍ ድረስ ስለዚህ ጉዳይ ለመጸለይ ቆርጦ ነበር። አንድ ጊዜ የምጸልይላቸው ብዙ ሰዎች ወይም ሁኔታዎች ነበሩ።በቃ ያ ብቻ ነው። ግን ደግሞ እግዚአብሔር ተናግሮን ለእነርሱ ወይም በእነርሱ ላይ ማድረግ የሚፈልገው ነገር እስኪፈፀም ድረስ እንድንፀልይላቸው ሰዎችን እንደሚመድብልን አምናለሁ። ስለ አንድ ሰው፣ ለሃያ-አምስት ዓመታት ጸልያለሁ፤ ደግሞም እስከምሞት ድረስ ወይም እግዚአብሔር እስኪለቅቀኝ ድረስ፣ ወይም ሰውዬው እስኪሞት ድረስ ወይም መሆን ያለበት ነገር እስኪሆን ድረስ እቀጥላለሁ። በእርግጥ ለዚህ ሰው መጸለይ የሰለቸሁባቸው ጊዜያት አሉ፣ ነገር ግን እኔ የሚሰማኝ ምንም ይሁን ምን አሁንም እራሴን እየጸለይኩ አገኘዋለሁ። እግዚአብሔር ይህንን ተልእኮ እንደሰጠኝ አውቃለሁ እናም ተስፋ አልቆርጥም! እግዚአብሔር የዚህን ግለሰብ ፍጻሜ ለማሳመር ጸሎቶቼን እየተጠቀመ እንደሆነ አምናለሁ።
ሌሎች ጊዜያት ደግሞ አሉ፣ከዚህ የበለጠ ልጸልይላቸው እንደሚገባኝ የተሰማኝ ነገር ግን እኔ የሚሰማኝ ምንም ይሁን ምን፣ ስጸልይ ወደ አእምሮዬ አይመጡም። ደግሞ ለመጸለይ እሞክር ይሆናል፣ ግን ፍላጎት የለኝም፣ ወይም ብዙ የምለው አይኖረኝም ደግሞም የምለው እንኳን ደረቅ እና ሕይወት አልባ ነው።
እግዚአብሔር ከተናገረህ ደግሞም ስለ አንድ ሰው ወይም ስለ አንድ ነገር እንድትጸልይ ተልእኮ ከሰጠህ፣ ለመጸለይ ፍላጎት ለማምጣት “መጣጣር” የለብህም፤ በልብህ እና በአዕምሮህ ውስጥ ታገኛቸዋለህ እናም ጸሎት ቀላል ይሆናል። እንዲያውም ይህን ለማድረግ ሳታቅድ እንኳን ለእነርሱ እየጸለይ ልትገኝ ትችላለህ። አንድ ሰው በልብህ ወይም በአእምሮህ ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ ከእግዚአብሔር እየሰማህ እንደሆነ እመን እና ጸልይ!
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ሁሉን ነገር ማድረግ እና ማንኛውንም ነገር በጥሩ መንገድ ማድረግ አትችልም፤ ስለሆነም ተልዕኮህን ፈልግ እና ወደ እግዚአብሔር እረፍት ግባ።