“ተመስገን” በል

“ተመስገን” በል

«ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ።» (1ኛዜና. 16፡34)።

ምስጋና የህይወታችን አንዱ ክፍል ሊሆን ይገባል። ምስጋና እግዚአብሔር ሊናገር የሚችልበትን ሥፍራ (ሁኔታ) ይፈጥራል፣ እርሱም የጸሎት አንድ ክፍል ሲሆን ንጹህና ቀላል የሆነ በተፈጥሮአዊ መንገድ ከእኛ የሚፈስ ሊሆን ይገባል። በየማታው ሁልጊዜ ጊዜ ወስደን በቀኑ ውስጥ እርሱ እኛን የረዳበትን ነገር እያሰብን እግዚአብሔርን ልናመሰግን እንችላለን። ነገር ግን በተጨማሪ እኛ በቀጣይነት ሁልጊዜ እርሱ በህይወታችን እየሠራ ያለውንና የባረከንን በረከት እየተመለከትን የምስጋና ጸሎት ከእኛ ሊወጣ ይገባል። ለምሳሌ፡ «ጌታ ሆይ ስለዛሬ ሌሊት መልካም እንቅልፍ አመሰግናለሁ» «እግዚአብሔር ሆይ ወደ ጥርስ ሐኪም ሄጄ ሊሆን ይችላል ብዬ እንዳሰብኩት ስላልተጎዳሁ አመሰግናለሁ» « አባት ሆይ በዛሬው እለት ስለወሰንኩት መልካም ውሳኔ እንድወስን ስለረዳኸኝ አመሰግናለሁ» ወይም «ጌታ ሆይ እንድበረታ ስለረዳኸኝ አመሰግናሁ»

እግዚአብሔር ሁልጊዜ ለእኛ መልካም ነው፣ ሁልጊዜም ታማኝ ነው፣ እንዲሁም ሁልጊዜ በሁሉም አስፈላጊው መንገድ ሁሉ በህይወታችን እኛን ሊረዳን በትጋት እየሠራ ነው። እኛም እርሱ ለእኛ እየሠራ ባለው ነገር ሁሉ ምላሽ እንዲሆን እርሱን ልናደንውና ልናመሰግነው ያስፈልጋል። እግዚአአብሔርን በልባችን በዝምታ ድምጽ ልናመሰግነው ይገባል እንዲሁም ከፍ ባለ ድምጽ ልናመሰግነው ይገባል ምክንያቱም እርሱ በመልካምነቱ የእግዚአብሔርን ፍቅር ለእኛ ስለገለጠልን ንቁና የተዘጋጀን እንድንሆን ይረዳናል።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ዛሬ እግዚአብሔርን ምንም ነገር ከመጸለይህ በፊት ስለሃያ ነገሮች እናመሰግነዋለን።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon