ተስማምታችሁ በመኖር ተስማምታችሁ ፀልዩ

የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና፡፡ ሮሜ 5 9

የስምምነት ፀሎት ውጤታማ የሚሆነው በፀሎት የተስማሙት ሰዎች በዕለታዊ የሕይወት ኑሮአቸው ተስማምተው ሁልጊዜ ሲኖሩ ነው፡፡ ተስማምተው መኖር ማለት የእራሳችን የሆነ አመለካከት አይኖረንም ማለት አይደለም፡፡ ያ ማለት ደግሞ ስምምነት የጋራ ክብርና መቀባበል በግንኙነት ውስጥ ያስፈልጋል፡፡ ያ ማለት መለያየትና ሁከት የሚያመጡትን እንደ ግለኝነት፣ ንዴት፣ ቅናት፣ መራሪነትና ውድድርን ማስወገድ ነው፡፡ አብሮ መኖር ማለት እንደ አንድ የኳስ ጫወታ ቡድን፡- ሁሉም ለአንድ ዓላማ አብሮ ይሰራል፡፡ እያንዳንዱ እየተረዳዳና እያበረታታ ይሠራል፡፡ ልክ እንደ ቡድን ጫወታው አማኞች በመቀባበልና በመተማመን ለአንድ ዓላማ ስኬት መቆም ይኖርባቸዋል፡፡

የስምምነት ፀሎት በጣም ኃይል አለው፡፡ ነገር ግን ውጤታማ የሚሆነው አብሮ በስምምነት ለመኖር ጥረት በሚያደርጉ ዘንድ ነው፡፡ ለምሣሌ አብዛኛውን ጊዜ እኔና ባለቤቴ ዴቭ የምጨቃጨቅና የምንታወክ ከሆነና ነገር ግን ብርቱ ጉዳይና አስቸኳይ ነገር ገጥሞን የስምምነት ፀሎት ለመፀለይ ብንፈልግ እንዲህ ዓይነት ፀሎት ውጤታማ አይሆንም፡፡ ያ ምክንያት እኛን የማስማማት ኃይል የለውም፡፡ በቅድሚ በስምምነት መኖር አለብን፡፡ ከሌሎች ጋር በሰላምና በአክብሮት ኑሩ፣ ለሰዎችና ለሁኔታዎች በማስተካከልና በመመቻቸት ሰላምን ለመፍጠርና የጠፋውንና የተበላሸውን ሠላምና ለመጠገን ለሰዎችና ለነገሮች እራስህን በማስተካከልና በማመቻቸት ኑር፡፡ (ሮሜ 12 16 ተመልከት)

ኅብረትን መፍጠርና ስምምነትን ማጠናከር ጥረት ይጠይቃል፡፡ ነገር ግን ይህ ኃይል የሚለቀቀው ሰዎች ሲፀልዩ ሲሆን ለዚህ ደግሞ የስምምነት ፀሎት ይጠቅማል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ነገሮችና ሁኔታዎች ከተመሰቃቀሉና እንዳልነበሩ ከሆኑ በኋላ መልሶ ማረጋጋትና ፀጥ እንዲል ማድረግ ቀላል አይደለም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon