ተስፋህን በተስፋ ጠብቅ

ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንድችል አጥብቆ እየተረዳ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም፡፡ ሮሜ 4 20

በዘፍ 17 16 እግዚአብሔር ለአብርሃም ወራሽ እንደሚሰጠው ተስፋ ሰጥቶት ነበር፡፡ ነገር ግን ችግራቸው አብርሃምም ሆነ ሳራ ሁለታቸውም አርጅተው በእርግጥም በጣም አርጅተዋል፡፡ እርሱ የመቶ ዓመት ሽማግሌ እርሷ ደግሞ የዘጠና አመት አሮጊት ልጅ የመውለድ ዕድሜአቸው በጣም ሄዶዋል፡፡ ነገር ግን አብርሃም እግዚአብሔር እንደተናገረው በተፈጥሮአዊ መልክ ከመውለድ ጊዜ ያለፈ ነው፡፡ ሆኖም የእርሱና የሣራ ልጅ የመውለድ ችሎታ የሚወሰነው በእግዚአብሔር ችሎታ እንጂ በሌላ ነገር ላይ እንዳደለ አውቀው አምነዋል፡፡ ስለዚህ እምነቱ በእግዚአብሔር ተስፋ ላይ በመትከል እምነቱን በእግዚአብሔር ላይ አድርጎ በምሥጋና በእርሱ ፊት እንደተመላለሰ ከዛሬ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍላችን እናነባለን፡፡

እንደገና መልሼ የምለው እንደተፈጥሮአዊ አነጋገር አብርሃም በጭራሽ ምንም ተስፋ የሚያደርግ ምክንያት አልነበረውም፡፡ በእርግጥም የሆነ ሁኔታ ከተስፋው ጀርባ ካለ ምናልባት ከዚህ በፊት ሁለት የዘጠና ዓመት እድሜ ያላቸው ሰዎች በተፈጥሮአዊ መንገድ (ባዮሎጂካዊ ልጅ) ወልደው የሚያውቁ ከሆነ፡፡ ሆኖም ግን አብርሃም በተስፋው ፀና የእግዚአብሔርን ተስፋ በማመን ፀና እምነቱን ተቃርነው እንደግርግዳ የቆሙትን በንቃት በመመልከትም ተስፋ ባለመቁረጥ ፀንቶ ቆመ፡፡ ምንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል የሞተና የሣራም ማኅፀን በእርግጥ የሞተ ቢሆንም አብርሃም የተፈጥሮአዊ እርግጠኛነት ላይ ተመስርቶ በእምነቱ ተስፋ አልቆረጠም ባለማመን መታበል ሳይናቃነቅ ቆመ እንጂ በእግዚአብሔር ተስፋ ላይ አላጉረመረመም እግዚአብሔርን በማመስገን በእምነቱ እያደገ ኃይሉን በእምነት አዲስ፡፡

እግዚአብሔር የተስፋ ቃል ሰጥቶህ እስካሁንም እንዲፈፀም እየጠበቀ ከሆነ ልክ እንደ አብርሃም በተስፋ ቃል ፀንተህ እያስታወስክ በምሥጋና ሆነህ ጠብቅ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- በምሥጋና ውስጥ በመሆን የተስፋ ቃልህን ፍጻሜ ተጠባበቅ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon