ተስፋ፡ በደስታ መልካም ነገሮችን መጠባበቅ

ተስፋ፡ በደስታ መልካም ነገሮችን መጠባበቅ

የምትዘገይ ተስፋ ልብን ታሳዝናለች የተገኘች ፈቃድ ግን የሕይወት ዛፍ ናት። – ምሳሌ 13፡12

ተስፋ ማለት “መልካም ነገሮችን በደስታ መጠባበቅ ነዉ” የሚል ፍቺ ሰጥቼዋለሁ፡፡ በህይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔርን መልካምነት ስንጠባበቅ ለትልቅ ደስታ በር ይከፍትልናል፡፡ ስለዚህ አንድ መልካም ነገር እንዲሆንልህ በፍጹም ተስፋ እያደረግህ ነዉ?

እኔና አናንተ በህይወት እስከኖርን ድረስ ሁልግዜም ወደ አንድ ቦታ እየሄድን ነዉ፡፡ እግዚአብሔር በግብ የምንመራ ባለራዕዮች አድርጎ ፈጥሮናል፡፡ ያለራዕይ ስልቹና ተስፋቢስ እንሆናለን፡፡ በምሳሌ 13፡12 መሰረት የምትዘገይ ተስፋ ልብን ታሳዝናለች ነገር ግን ፍላጎታችን ሲሟላ የህይወት ዛፍ ነዉ፡፡

ህይወትን እንድናጣጥም እግዚአብሔር በእርሱ ተስፋ እንድንኖር ይፈልጋል፡፡

ተስፋ ከሌለህ ደስተኛ መሆን አትችልም፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ ባደረግህ ቁጥር ደስተኛ እየሆንክ ትመጣለህ፡፡ ተስፋ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል ባይ አዉንታዊ ነዉ፡፡ ህይወትን ለማጣጣም በተስፋ የተሞላ መልካም አመለካከት መያዝ አለብህ፡፡ አግዚአብሔር አዉንታዊ ነዉ ደግሞም በእያንዳንዳችን ህይወት አዉንታዊ ነገሮች እንዲከሰቱ ይፈልጋል ስለዚህ ዛሬ ራስህን በእርሱ ተስፋ ሙላና መልካም ነገሮችን በደስታ በመጠባባቅ ኑር፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ዛሬ በህይወቴ የአንተን መልካምነት በደስታ መጠባበቅን መርጬአለሁ፡፡ ተስፋዬ ሲጨምር ደስታዬም እንሚጨምር አዉቃለሁ፡፡ ጌታ ሆይ ተስፋዬን በአንተ ላይ አደርጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon