እምነት ተስፋ ያደረግነው ነገር እንደሚፈጸም ርግጠኛ የምንሆንበት፣ የማናየውም ነገር እውን መሆኑን የምንረዳበት ነው። – ዕብራዊያን 11፡1
ስለ የወደፊት ሕይትህ ስታስብ ተስፋ አለህ? ወይስ ስጋት/ ፍርሃት ይሰማሃል?
የእግዚአብሔርን ታማኝነት በሕይወታቸው ያዩ ሰዎች ስለ ወደፊት ሕይወታቸው ታላቅ ተስፋ ይስማቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች አስቸጋሪ ሁኔታዎች በደቂቃዎች ውስጥ ወደ አስደናቂ ምስክርነቶች ሊቀየሩ እንደሚችሉ ያውቃሉ፡፡ በሌላ መልኩ ተስፋ በማጣት ውስጥ ያሉ ሰዎች ሕይወት ከተስፋ ቢስነት አቅጣጫ ያዩቷል፡፡ ለፍርሃት የቅርብ ጓደኛ የሆነው ተስፋ ቢስነት መደበኛ ሕይወትን በደስታ እንዳይኖሩ ያደርጋል ብሎም የወደፊቱን አስመልክቶ በጭንቀት እንደሞሉ ያደርጋቸዋል፡፡
ተስፋ የፍርሃት ተቃራኒ ለእምነት ደግሞ የቅርብ ዘመድ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስናምን ፤ ማመናችን ወደ ተስፋ ይመራናል በተጨማሪም የወደፊቱን አስመልክቶ አመለካከታችንም ቀና ይሆናል፡፡
ተስፋ ያልተመለሱልን ጥያቄዎች በእግዚአብሔር እጅ እድናስቀመጥ ይረዳናል ፤ በሰላም እንድንቀመጥ እና መጪው ቀናችን በጎ እንደሆን እድናምን ያስችለናል፡፡
በእግዚአብሔር ፍቅር ስናምን ተስፋ ይኖረናል፡፡ እርሱ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሊመራን እና የሚያስፈልገንን ሊያደርግልን ኃይል አለው፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚብሔር ሆይ በአንተ መታመን ወደ ተስፋ ይመራልና በአንተ ለመታመን መርጫለሁ፡፡ በአንተ ተስፋ አድርጌያለሁና አንተም እኔን መንከባከብ ስለምትችል መፍራት አልፈልግም፡፡