እንግዲያስ እያንዳንዳችን ስለራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን፡፡ – ሮሜ 14፡12
ብዙ ሰዎች ሌሎች ሰዎችን ለማስደሰት የተጠመዱ በመሆናቸው የእግዚአብሔርን ዓላማ በማሳካት ረገድ በፍፁም ስኬታማ አይደሉም፡፡ ይህች ዓለም በህይወታችሁ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ አውቃለሁ በሚሉ ሰዎች የተሞላች ናት፡፡
ነገር ግን መፅሀፍ ቅዱስ ሲናገር እንዴት እንደኖራችሁ መልስ የምትሰጡት ለእግዚአብሔር ነው፣ እንጂ ለሌላ ለማንም አይደለም፡፡ ለዚህ ነው በእያንዳንዱ ቀን ድርሻችንን ተወጥተን እግዚአብሔርን የሚያስደስት ነገር ለማድረግ ፀጋው መኖር ያሚያስፈልገን፡፡
መንጋውን ከመከተል ይልቅ ልባችሁን ለመከተል በብርቱ ፈልጋችኋል? ብዙ ድምፆች ከዓላማችሁ ሊያሰናክሏችሁ ሲሞክሩ እናንተ ግን በክርስቶስ ላይ ትኩረታችሁን ታደርጋላችሁ?
በዚህ ምድር ላይ ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ፡ እነርሱም የሆነ ነገር እንዲፈጠር የሚጠብቁ እና ነገሮች እንዲፈጠሩ የሚያደርጉ ሰዎች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር የጠራችሁ ለመንግስቱ ታላቅ ነገርን እንድታደርጉ ነው፤ እርሱም ዓላማችሁን ለመፈፀም በክርስቶስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ነገር ሰጥቷችኋል፡፡
ስለዚህ ከልባችሁ ሁኑና ህይወትን በዓላማ ኑሩ፡፡ እያንዳንዱ ሰው የሚያደርገውን ነገሮች ለማየት ጠብቃችሁ ስታበቁ መንጋውን አትከተሉ፡፡ ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፣ ውሳኔ ወስኑ እናም ተንቀሳቀሱ!
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ! ህይወቴን ሌላውን ለማስደሰት ሳይሆን፣ አንተን ለማስደሰት መኖር እፈልጋለሁ፡፡ ጠንከር ብዬ አንተ ለእኔ ያለህ ዓላማ ውስጥ መግባት እፈልጋለሁ፡፡ ወደኋላ አልመለስም፤ ነገር ግን ህይወቴን ለአንተ በዓላማ እኖራለሁ፡፡