እንግዲህ በእኛ እንምሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ልናደርግ ሰምቻለው፡፡ ኤፌ 3 20
አንዳንድ ሰዎች መጥፎ ዜናን መስማትና ለጥሩ ዜና መፀለይን ይፈራሉ፡፡ ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር ባሕሪ አይደለም፡፡ የእግዚአብሔርን ድምፅ ለመሥማትና የእርሱን ኃይል በሕይወታችን ሲለቀቅ ለማየት ከፈለግን እርሱን የሚያስደስት ማንነትና ሕይወት ሊኖረን ይገባናል፡፡ በባሕሪያችን ከክፉ ይልቅ መልካም እይታ ሊኖረን ያስፈልጋል፡፡ በመሠረቱ የሕይወታችን አቀራረብና መርህ በእምነትና በተስፋ የተሞላና መልካም እይታ የሕይወታችን ዘይቤ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ያለ እምነት እግዚአብሔርን ማስደሰት አይችልም፡፡ (ዕብ 11 6 ተመልከት) እንዲሁም ተስፋችን ደግሞ አያሳፍረንም፡፡ (ሮሜ 5 5) ተመልከት እግዚአብሔር ሁልጊዜ መልካም እንጂ በእርሱ ዘንድ ክፋት የለም፡፡ በማንነቱም ሆነ በድርጊቱ በእርሱ ዘንድ ክፋት የለም፡፡ እርሱ የሚያደርገው ሁሉ ነገር መልካም ነው፡፡ ለዚህም ነው እንደፀለይነው እንደዚያው የምጠብቀው፡፡ ከፀለይን በኋላ መጨነቅ የለብንም፡፡ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር እራሱ ቢያደርግ እንኳ እኛ ከፀለይነው ወይም ከጠየቅነው በላይ እጅግ አብልጦ ያደርጋል ብለን መታመን አለብን፡፡
ለዛሬ ቀን ጥቅስ የምለው ‹‹እግዚአብሔር ታላቅና አብዝቶ ከሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነገር ከለመነውና ካሰብነው አብልጦ ከፀሎታችን፣ ከፍላጎታችን፣ ከሃሳባችንና ከሕልማችን በላይ ያደርጋል፡፡›› የሚገርመው ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ በድፍረትና በመተማመን እንድንፀልይ ያበረታታናል፡፡ እኔ በግሌ ትላልቅ ፀሎቶችን በመፀለይ በትልቅ ተስፋ በመጠባበቅ የፀለይኩትን በግማሽ እንኳ ቢሆን እንኳ ባገኝ ይሻለኛል እንጂ እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ ለሚመልሰው ትናንሽ ፀሎቶች ውጤት መጠበቅ አልፈልግም፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ታላላቅ ነገሮችን ከእግዚአብሔር ጠብቅ