ታቦቱን ተከተል

ሕዝቡን፦ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት።ኢያሱ 3:3

ሁን በፊትህ አዲስ እድል እያጋጠመህ ነው? ማንኛዉም ዓይነት ዕድል ይሁን ታቦቱን መከተል ጠቃሚ ነዉ፤ ይህንን ስል ምን ማለቴ ነዉ? አንዳንድ ጊዜ ስለተላመድንና ስለተመቹን ብቻ አሮጌ ነገሮችን ልንይዝ እንችላለን እናም ወደ ሌላ ያልተሰመረ ድንበር መሄድ እንፈራለን፡፡ አንዳንድ ጊዜ  አዲስ ነገር አይተን እርምጃ መዉሰድ የምንችልበት ጊዜ ደግሞ አለ እንድናደርገዉ የእግዚአብሔር ጊዜ ከመድረሱም በፊት፡፡

በኢያሱ 3፡3 እግዚአብሔር እስራኤላዊያን የቃል ኪዳኑን ታቦት እንዲከተሉ ተናግሯል፡፡ ታቦቱ የእግዚአብሔርን ቅባት ይወክላል፣ የእግዚአብሔርን መገኘት፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ፡፡ የእኛን ወይም የሌሎች ሰዎችን ፈቃድ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድ መከተል መማር ለእኛ ጠቃሚ ነዉ፡፡

እግዚአብሔር ለእናንተና ለእኔ ዕቅድ አለዉ፤ ያ ዕቅድ ሳይበላሽ የማያዉ ብቸኛዉ መንገድ የራሳች8ንን ሰጋ እና ስሜት ወይም የሌሎች ሰዎችን ሳይሆን ታቦቱን ወይም የእግዚአብሔርን ፈቃድ መከተል ነዉ፡፡

አስታዉስ ዛሬ የእግዚአብሔር ፈቃድ በህይወትህ ላይ ምንም ዓይነት ይሁን የምትፈጽምበትን መንገድ ያቀርብልሃል፡፡ 

የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ልክ እንደ እስራኤላዊያን ታቦቱን መከተል እንደሚያስፈልገኝ  አዉቄአለሁ፡፡ ለአዳድ እድሎች የእኔ ጊዜ ሳይሆን ያአንተ ፈቃድ ወሳኝ ነዉ፡፡ አንተን መከተል ስጀምር እቅድህን ወደ ህይዎቴ ለማምጣት መንገድ እንዳለህ አዉቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon