ትንንሽ ነገሮችን ማስተዋል

ትንንሽ ነገሮችን ማስተዋል

ስለዚህ በእርግጥ አሁን እንደምታደርጉት ሁሉ እርስ በእርሳችሁ ተጽናኑ፤አንዱም ሌላውን ያንጽ፡፡ – 1 ኛ ተሰ 5፡11

ንድ ቀን ወደ አንድ ቢሮ ህንጻ እየገባሁ ሳለሁ በአቅራቢያው የቆመ አንድ ሰው በሩን ከፈተልኝ፡፡ ፈገግ ብዬ አመሰገንሁት፡፡

“በር የከፈትሁለት አምስተኛው ሰው ነሽ ግን ፈገግ ያልሽልኝ የመጀመሪያዋ ያመሰገንሽኝ ደግሞ ሁለተኛዋ ሰው ነሽ” አለኝ፡፡

ለሁለተኛ ጊዜ ፈገግ ብዬ አመሰገንሁት፡፡ካለፈ በኋላ ግን ሌሎችን ለማናውቀው ሰው በር እንደመክፈት ባለ ትንንሽ ነገሮችም እንኳ ቢሆን እንዴት እንደ መብታችን እንደምንቆጥራቸው አሰብሁ፡፡

ብዙ ጊዜ ሰዎችን የምናመሰግነው ትልቅ ነገር ሲያደርጉልን ነው፡፡ ግን ምን ያህል ነው ስለ ትንንሽ ነገሮች የምንመሰግነው?

አንድ ሰው አንድን መልካም ነገር አድርጎላችሁ ስታመሰግኑ ይገነባቸውና ያበረታታቸዋል፡፡ ቢሮው ህንጻ ጋር እንደነበረው ሰውዬ ሁሉ ለእነርሱ ያ ብዙ ማለት ነው፡፡

ዛሬ የምትጠብቁት ባስ በሰአቱ ነው የመጣው? ከሆነ ሹፌሩን አመሰገናችሁት? ለመጨረሻ ጊዜ ምግብ ቤት ስትመገቡ ሳጠይቅ ለሁለተኛ ጊዜ ቡና ስለቀዳላችሁ አስተናጋጁን አመስግናችሁታል? ላስረዳችሁ የፈለግሁት ነጥብ ይሄ ነው፡በህይወታችሁ ያሉትን ሰዎች የሚያመሰግን አመለካከትን አዳብሩ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ ሰዎች የሚያደርጉልኝን ትንንሽ የሚረዱኝ ነገሮች እንዳስተውል ንቁ አድርገኝ፡፡ የማላመሰግን መሆን አልፈልግም፡፡ላመሰግናቸው እና ላበረታታቸው እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon