እግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና:: – ሮሜ 14፡17
ሮሜ 14:17 የእግዚአብሔርን መንግሥት ሲገልጸው በመንፈስ ቅዱስ የሆነ መልካምነት፣ ሰላምና ደስታ ያለበት ሕይወት ነው ይላል፡፡ መንግስቱን መፈለግ አለብን፡፡ ነገር ግን ብዙ ሰዎች ሕይወታቸውን የሚያባክኑት ሌሎች ነገሮችን በመፈለግ ነው፡፡ ሌሎች ነገሮችን በመከተል የተጠመዱ ስለሆነ ጽድቅን፣ ሰላምንና ደስታን በተመለከተ ግን ምንም ፍላጎት አያሳዩም፡፡
ዓለማዊ ነገሮች ሁሉ ቢኖሩኝ በሕይወቴ ምንም ዓይነት ጭንቀት አይኖርም ሕይወቴም በሰላም የተሞላ ይሆናል ብዮ አስብ ነበር፡፡ ነገር ግን ምንም ያህል ነገር ቢኖረኝ ሰላምን ሊገዛልኝ አልቻለም፡፡ እውነተኛ ሰላም የሚመጣው ከእግዚአብሔር ጋር ኀብረት በማድረግ ብቻ ነው፡፡
ይህንን መረዳት በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም እውነተኛው ሃብት በክርስቶስ ውስጥ ሆኖ ሳለ አብዛኛው ክርስቲያን ሙሉ ሕይወታቸውን የሚያውሉት ትክክለኛ ያለሆነውን ነገር በመፈለግ ነው፡፡ ዛሬ የምትፈልጉት ነገር ምን ይሆን? ለአንተ ሃብትህ ምንድን ነው? የዚህ ዓለም ነገር መጨረሻው ያልረካህ ሰው አድርጎ ነው የሚተውህ፡፡ እግዚአብሔርንና የእርሱን ጽድቅ፣ ሰላምና ደስታ ብትፈልግ ግን እግዚአብሔር እንድትኖር የሚፈልገውን የረካና የተከናወነ ሕይወት በተሟላ ሁኔታ ትኖራለህ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሊዘህ ሕይወት ኑር፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ከዛሬ ጀምሮ እርካታ የሌለባቸውን ዓለማዊ ነገሮችን መከተል አቁሜ ከአንተ ጋር መሆን፣ የአንተን ጽድቅ፣ ሰላምና ደስታ እፈልጋለሁ፡፡