ትክክል እንድትናገር ትክክል አስብ

ትክክል እንድትናገር ትክክል አስብ

አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል። – ያዕ 3፡6

አሉታዊ ንግግር የሚጀምረዉ በአሉታዊ ሀሳብ ነዉ፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰራተኛ የሚሰራበት ድርጅት ሰራተኛ ሊቀንስ ነዉ የሚል ጉምጉምታ ቢሰማ እንድህ ያስባል ሁል ጊዜ ጥሩ ነገር ሲጀምር መጥፎ ነገር ይከሰታል፤ ከዛም ምንአልባት ሥራዬን አጣለሁ ይላል፡፡

ቃላቶቼ አሉታዊ እንዲሆኑ ያደረገ አሉታዊ አስተሳሰብ ነበረኝ ያም ሁሉ በህይወቴ ተንጸባርቋል፡፡ በመጨረሻም መንገዴን ለመቀየር ወሰንሁ አሉታዊ አስተሳሰብም አቆምኩኝ፡፡ ከጊዜ በኋላ አሉታዊ ካለመናገር የዘለለ መስራት እንደሚያስፈልገኝ አስተዋልኩኝ ፤ አሉታዊ አስተሳሰብ ማስወጣት ብቻ በቂ አይደለም ፤ አዉንታዊ ማሰብ መጀመር ነበረብኝ፡፡

አዉንታዊም ሆነ አሉታዊ አስተሳሰባችን ነገአችንን የሚቀርጽ ቃል እንድንናገር ያደርገናል፡፡ የተሳሳተ ነገር ስንናገር በሕይወታችን እሳት ሊሆን ይችላል (ያዕ 3፡6ን ተመልከት)፡፡

ነገር ግን ከመጀመሩ በፊት ትክክል የሆነዉን በመናገር እሳቱን ማስቆም እንችላለን ፤ ደግሞም ትክክል ብቻ መናገር የምንችለዉ ትክክል ስናስብ ነዉ፡፡ በመንፈስ ቅዱስና በእግዚአብሔር ቃል እንድትሞሉ አነሳሳችኋለሁ፡፡ አስተሳሰቦችህን እርሱ ይቆጣጠር ፤ ወደ አዉንታዊ ቃላት የህይወት ዘይቤም ይምራህ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! በቃልህ ተመስርቼ አዉነታዊና ህይወት ሰጪ ቃላት መናገር እፈልጋለሁ፡፡ አንተን በአንደበቴ ቃል ማክበር እንድችል የእየሱስን አእምሮ፣ የታደሰ አእምሮ እፈልጋለሁ ወደ ሀሳቦቼ እጋብዝሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon