ትጋት/ጽናት ዋጋ ይከፍላል

ትጋት/ጽናት ዋጋ ይከፍላል

ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል። – ማቴ 19፡29

አገልግሎታችንን በጀመርንባቸው የመጀመሪያ አመታት፣ እኔ እና ዳዊት በተለያዩ በርካታ አስቸጋሪ ፈተናዎች ውስጥ አልፈናል፡፡ እኔ በአስተሳሰቤ/ አመለካከቴ ላይ መስራት ነበረበኝ፡፡ በትዳራችን ላይ እና ገንዘብን እንዴት መያዝ እንዳለብን መስራት አስፈልጎን ነበር፡፡

ለስድስት ዓመታት ካልሲዎቼንና የውስጥ ልብሶቼን ምገዛው ከውራጅ ተራ ነበር፡፡ ሙሉ ለሙሉ የወረደ ሕይወት እየኖን እግዚአብሔር በሕይወታችን ስለሚያደርገው የተትረፈረፈ አቅርቦት እያስተማርኩ ነበር፡፡ይህ ብቻ አይደለም ፣ በዚያ ግዜ የሴቶች መስበክ ብዙም የተለመደ አልነበረም፡፡ ወዳጆቻችንን አጣን፣ የቤተሰብ አባሎቻችንም ከእኛ ጋር ምንም ዓይነት ነገር ማድረግ አይፈልጉም ነበር፡፡

በቃ በጣም ከባድ ነበር እንደውም አንዳንድ ጊዜ ለማቋረጥ ይቃጣኝ ነበር፡፡ ዛሬ ግን በመላው ዓለም በጣም በርካታ ሰዎች በአገልግሎታችን ጌታ ባደረገው ነገር ስለተገለገሉ ከእግዚአብሔር ጋር ተጣብቄ በመቀጠሌ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ በማቴ 19 ላይ እርሱን ለመከተል ስናስብ “አስፈላጊ” የሚባሉ ነገሮችን መተው እንዳለብን ይናገራል፡፡ በወቅቱ እንዲኖረን የፈለግነው ነገር ሁሉ አልነበሩንም፡፡ ነገር ግን አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንኳ ከእግዚአብሔር ጋር የምታደርጉትን ጉዞ በመጽናት ቀጥሉ፡፡ በእርሱ ላይ አተኩሩ፡፡ እግዚአብሔር ለአንተያ ባዘጋጀው ድል ስትለማመዱ ያኔ ይከፈላችኋል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ፣ አንዳንድ ጊዜ በክርስትና ሕይወት መጽናት ከባድ ይሆናል፡፡ ጽናት እንደሚከፍል አውቃለሁ፡፡ በርምጃዮ እንዲቀጥል የሚያስፈልገኝን ጉልበት ስለምትሰጠኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ አንተን ብቻ እከተላለሁ፡፡ ምክንያቱም ዋናው ነገር አንተ ብቻ ስለሆንክ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon