ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ። – 2 ቆሮ 3:17
ፍቅር ነጻ አዉጪ ነዉ፡፡ አባል የመሆንና የነጻነትን ስሜት ይሰጣል፡፡ ፍቅር ሁሉን ለመቆጣጠርና የራሱን ፍላጎት ለማሟላት በሌሎች ለመጠቀም አይሞክርም፡፡
ኢየሱስ ከአብ ዘንድ የተላከዉ ነጻነትን ለማወጅ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ እንደ አማኞች ልናደርገዉ የተገባዉ ተመሳሳዩን ነዉ፤ ሰዎች እግዚአብሔር በህይወታቸዉ ያለዉን ፈቃድ እንዲያሟሉ ነጻነት መስጠት እንጂ እነርሱን በቁጥጥራችን ውስጥ እንዲሆኑ ማምጣት አይደለም፡፡
እኔ ሰዎች እንዲያደርጉ የምፈልገዉን ነገር እንዲያደርጉ ስሞክር እግዚአብሔር ለልቦቻቸዉ የሚናገርበትን በር እየዘጋሁ እንደሆነ ደርሼበታለሁ፡፡ ሰዎች ለእግዚአብሔር ክብር እንጂ ለራሳችን ፍላጎት እንዳይሆኑ ልንለቃቸዉ ያስፈልጋል፡፡
ሰዎችን ነጻ ልቀቁአቸዉ ይህንን ስታደርጉ ይወዱአችኋል፡፡ ሰዎችን የምትበዘብዙ አትሁኑ በምትኩ እግዚአብሔር እንዲቆጣጠራቸዉ መተዉን ተማሩ፡፡
ትልቅ ፍቅር አለዉ የሚባል ሰዉ ሰዎችንና ነገሮችን ነጻ ለመልቀቅ የሚችል ሰዉ ነዉ፡፡ ዛሬ መቆጣጠር የሚወድ ሰዉ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ብቻ የሚመጣዉን ነጻ አዉጪ ፍቅር በነጻ የምትሰጥ ሰዉ ሁን፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ! አንተ ለእኔ የሰጠኸኝን ነጻ አዉጪ ፍቅር ለሌሎች መስጠት እፈልጋለሁ፡፡ ለመቆጣጠርና ለመበዝበዝ የሚመኘዉን ፍላጎቴን ጥዬዋለሁ፡፡ በሕይወቴ ያመጠሃቸዉን ሰዎች እወዳቸዋለሁ ለአንተም አደራ አሳልፌ እሰጣለሁ፡፡