ንዴታችሁን አያያዝ

ንዴታችሁን አያያዝ

የሞኞች ቁጣ በዕቅፋቸ ውስጥ ስለሆነ፣በመንፈስህ ለቁጣ አትቸኩል፡፡ – መክ 7፡9

ምክንያቱ ምንም ሆነ ምን ማንኛውም ንዴት በህይወታችን ላይ የሚያመጣው ተጽዕኖ አንድ ነው፡፡ ያናድደንና ጫናው እንዲሰማን ያደርገናል፡፡ውስጣችን ቆልፈን ንዴት እንደሌለብን ማስመሰሉ ደግሞ ለጤናችን ሁሉ አደገኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙውን ጊዜ እራሳችንን ብቻ ነው የምንጎዳው ያናደደን ሰው ጭራሽ አያውቅም፡፡

እንዴት አድርጌ እንደማሸንፈው እግዚአብሔር እስከሚያሳየኝ ድረስ የምታገለው ሀይለኛ ንዴት ነበረብኝ፡፡ንዴቴን የምይዝበት አዎንታዊ መንገድ በሂደት ተማርኩ፡፡ያ ለእኔ የአዲስ ጅምሮ ቦታ ነበር፡፡

ንዴት ሲያጋጥማችሁና በእግዚአብሔር መንገድ ልትፈቱት ስታስቡ ታሸንፉታላችሁ፡፡መንፈስ ቅዱስ የተረጋጋንና በመንፈስ ፍሬ የምንመላለስ ሰዎች እንድንሆን ይረዳናል፡፡ በህይወታችን ውስጥ ፍትህን ያጣመሙብንን ሰዎች ይቅር የምንልበት እና ሊወደዱ የማይችሉትን የምንወድበት ሀይል አለን፡፡

ለንዴታችን ሀላፊነት መውሰድ እና እንዴት ማስተካከል እንዳለብን መማር አለብን፡፡ ውስጣችን ከማጠራቀም ይልቅ ጌታን መፈለግ እና እንድታወጡት እንዲረዳችሁ መጠየቅ ይሻላል፡፡ በስርአቱ አስወጡት እናም ያ ጫናችሁን ያቀልላችኋል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ በውስጤ ምንም ንዴት መያዝ አልፈልግም ምክንያቱም ሞኝነት እና አንተን የማያስደስት ስለሆነ፡፡ በህይወቴ ያለውን ንዴት እንዳሸንፈው የአንተን እርዳታ እጠይቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon