ንጹህ ሕሊና እንዲኖር ማስተዋል ቁልፍ ነው

ንጹህ ሕሊና እንዲኖር ማስተዋል ቁልፍ ነው

ስለዚህ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ንጹሕ ኅሊና እንዲኖረኝ ሁል ጊዜ እጥራለሁ። – ሐዋ 24፡16

የጸጸትን ያህል ሕይወትን በደስታ እንዳናጣጥም የሚያደርገን ነገር የለም በመሆኑም ሕሊናችንን በንጽህና መያዝ ወሳኝ ነው፡፡ በሐዋሪያት ስራ መጽሀፍ ጳውሎስ ከዐለም መሻት በጸዳ መልኩ በሰው እና በእግዚአበሔር ፊት ንጹህ ሕሊና እንዲኖረኝ እጥራለሁ ይላል፡፡ ይህም መርህ ለእኛም ይሰራል፡፡ በንጹህ ሕሊና ጋር መሄድ ነጻ እና ደስተኛ መሆን ያስችለናል፡፡

ትክክል እና ትክክል ያልሆኑ ነገሮችን አስመልክቶ ነገሩ ምናልባት ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን ግልጽነት በሌላቸው የሕይወት አቅጣጫዎች? እየመረጥን ያለነው ጉዳይ ትክክል ወይም ትክክል ያልሆነ መሆኑን እርግጠኞች ሳንሆን እንዴት አድርጎ ንጹ ሕሊና ይኖረናል? ሳናገናዝበው በሀጢኣት ብንገኝስ? ከእግዚአብሔር የሆነ ማስተዋል ለዚህ ችግር መፍትሄ ነው፡፡

መለየት መንፈሳዊ መረዳት ነው፡፡ በንጹ ሕሊና ለመኖርም ቁልፍ ነው፡፡ ልምምድ የሚጠይቅ ነው፡፡ግን በቀላሉ ልባችንን ማዳመጥ ነው የሚያስፈልገን። እግዚአብሄር ወደ ፊት ጸጸት ሊያመጣብን ነገሮችን እንዳናደርግ ያሳውቀናል።

ሕሊናችሁን ንጹህ አድርጋችሁ እንድትኖሩ አበረታታችኋለሁ፡፡ ማድረግ የሌለባችሁን ነገሮች አታድርጉ፡፡ የማታውቁት ነገር ገጥሟችሁ እንደሆነ በእግዚአበሔር ማስተዋል ተደገፉ ፤ እርሱ ፈጽሞ ወደ ክፋት አይመራችሁም፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚብሔር ሆይ ስለማስተዋልህ አመሰግንሃለሁ ፤ ለልቤ የምትናገርበትን ረጋ ያለውን የቀስታ ድምስ እንደሰማ እርዳኝ ፤ እኔም ሕሊናዬን አንጽች በፊት ልኑር፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon