አልፈህ ሂድ

አልፈህ ሂድ

አዎን፣ በሞት ጥላው (ጥልቅ፣ ፀሐይ በሌለው) ሸለቆ ውስጥ ባልፍም፣ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህ [ለመጠበቅ] እና ምርኩዝህ [ለመምራት]፣ እነሱ ያጽናኑኛል። (መዝሙር 23:4)

ብዙ ጊዜ “በምን ውስጥ እንደምናልፍ” እንናገራለን፤ ነገር ግን መልካም ዜናው እያለፍን ነው፣ መውጫ በሌለበት በችግራችን ውስጥ ተይዘን አልቀረንም። እግዚአብሔር ከችግር ነፃ የሆነ ሕይወትን በጭራሽ አይሰጠንም፣ ነገር ግን ከእኛ ጋር እንደሚሆን እና ፈጽሞ እንደማይጥለን ወይም እንደማይተወን ቃል ገብቷል። እግዚአብሔር በአንድ ነገር ውስጥ ሲያሳልፈን ለወደፊቱ የምንጠቀምባቸውን ጠቃሚ ትምህርቶች ሁልጊዜ ያስተምረናል።

ከእግዚአብሔር ለመስማት በጣም ወሳኝ ከሆኑት ጊዜያት አንዱ በችግሮች ውስጥ በምናልፍበት ጊዜ መመሪያን ፍለጋ ነው። ምን ማድረግ አለብን? ችግሩ ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል? የዛሬው መዝሙር በምንሄድበት እግዚአብሔር እንደሚመራን ይናገራል። እግዚአብሔር እንደሚረዳን ማመን በችግሮቻችን መካከል ተስፋ ከመቁረጥ ይጠብቀናል።

የዕብራውያን መጽሐፍ መጨረሻ ላይ የተስፋችን ፍፃሜ እውን መሆን እንዲችል እግዚአብሔር በሁሉም በኩል እንድናልፍ እንደሚፈልግ ይናገራል (ዕብራውያን 6፡11ን መልከት) ።

ሰይጣን ተስፋ እንድንቆርጥ እና እንድናቆም ይፈልጋል፣ ነገር ግን እግዚአብሔር አልፈን እንድንሄድ ኃይልን ይሰጠናል! ነገሮችን የሚጀምር ነገር ግን ሁኔታዎች ሲከብዱ የማይጨርስ ሰው አትሁን። አንድን ነገር ስንጀምር ሞኞች እንዳንመስል የሚጠይቀንን ዋጋ መተመን እና ለመጨረስ የሚያስፈልገን እንዳለን እርግጠኛ መሆን አለብን። ቁርጠኝነት ለማጠናቀቅ የሚጠይቀን ነገር ነው – ሁሉም ጥሩ የሆኑ ስሜቶች ከጠፉ በኋላ እና ሌሎች ተስፋ ከቆረጡ በኋላም መቀጠል መቻል ማለት ነው። እስከ መጨረሻው አልፈህ ከሄድክ የእምነትህን ሽልማት ትቀበላለህ።


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ በሕይወት ሸለቆዎች ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ይመራሃል ደግምም ያጽናናሃል።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon