አመለካከት ፍጻሜን ይወስናል

አመለካከት ፍጻሜን ይወስናል

«አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና» (ምሳ.4፡23)።

አመለካከት እጅግ በጣም አስፋለጊ ነገር ነው፣ አመለካከታችን ወደ ውጪ እኛ የምናሳየውን ባህሪያችን ሆኖ ይታያል። አመለካከት መልካም ይሁን ክፉ ከሃሳባችን ይጀምራል። በጣም የታወቀ አባባል እንዲህ ይላል « ሃሳብህን ዝራው፣ ተግባርን ታጭዳለህ፤ ተግባርን ዝራው፣ ልምድን ታጭዳለህ፤ ልምድን ዝራው ባህርይን ታጭዳለህ፤ ባህርይህን ዝራው ፍጻሜህን ታጭዳለህ» ይላል።

ፍጻሜ የህይወት ውጤት ነው፤ ባህርይ ማለት እኛ ማን ነን፣ ልምድ ማለት የባህርይ የአስተሳሰብ የተወሰነ ማንነት ነው። ፍጻሜያችን ወይም የህይወታችን ውጤት የሚገኘው በትክክል ከሃሳባችን ነው። ይህ ደግሞ የህይወታችን ሁለንተናዊ ሂደት የሚጀምርበት ሥፍራ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን ለሁሉም አዕምሮአችን መታደስ አዲስ አመለካከትና አስተሳሰብ ማጎልበት ነው (ሮሜ 12።2፣ ኤፌ 4።23)። እኛ የእግዚአብሔር ቃል መልካም ተማሪ ስንሆን በእርሱ አዲስ የአስተሳሰብ አድማስ በውስጣችን ያድጋል። እርሱ ደግሞ የህይወታችን ውጤት የሆነውን የህይወታችንን አጠቃላይ ፍጸሜ ፍጹም ይለውጠዋል።

መጥፎ አመለካከት ማለትም መራርነት፣ ቁጣ፣ ይቅር አለማለት፣ ተነሳሽነት ማጣት፣ ብልግና፣ በቀልን ፍለጋ ወይም የማያመሰግን መሆን እና መዘርዘር ይቻላል እነዚህ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ህይወት እንዳይሠራ ሊከለክሉ ይችላሉ። መንፈስ ቅዱስ በመንፈሳዊ አመለካከት ውስጥ እንጂ በዓለማዊ አመለካከት ውስጥ መፍሰስ አይችልም።

በዛሬው እለት እንደመረጥነው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አመለካከትህን በየጊዜው መገምገምና በትጋት ልትጠብቀው ይገባል። አመለካከትህን መለወጥ ካስፈለገህ ሁሉንም አስተሳሰቦችህን መለወጥ ይገባሃል። ሰይጣን ሁልጊዜ አዕምሮአችንን በተሳሳተ አስተሳሰብ ለመሙላት ይጥራል። እርሱ ሊሰጠን የሚፈልገው የተሳሳተ ነገር ሁሉ መቀበል አይገባንም። ትንሽ ማንኪያ የምታክለውንንና ሊመርዘኝ የሚችለውን መርዝ አንድ ሰው ቢያቀርብልኝ አልቀበለውም፣ አንተም አታደርገውም። መርዝን ላለመቀበል እኛ ንቁዎች ከሆንን ሰይጣንም አዕምሮአችን ውስጥ መርዝ በመጨመር አስተሳሰባችንና አመለካከታችንን እንዲሁም ፍጻሜያችንን እንዳይመርዘው ነቅተን በመጠበቅ ልንከለክለው ይገባል።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ አመለካከትህ በትክክለኛ ሁኔታ ላይ እንዳለ እርግጠኛ ለመሆን በየዕለቱ አመለካከታችንን እንፈትሽ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon