አመስጋኝነትን መለማመድ

እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፤ ምስጋናውም ዘወትር ከአፌ አይለይም፡፡ – መዝ 34፡1

ኛ ሁላችን ለብዙ በረከቶቻችን ማመስገን እንዳለብን እናውቃለን፡፡ አግዚአብሔር በቃሉ አመስጋኝ እንድንሆን ነግሮናል እኛም ከልምዳችን በቁም ነገር ማመስገን እስንጀምር ሸክሞቻችንና ችግሮቻችን ከትከሻችን ላይ እንደሚቀሉን እናውቃለን፡፡

ዳዊት ሲናገር እግዚአብሔር አምላኬን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፤ ምስጋናው ዘወትር ከአፌ አይለይም…የጻድቅ መከራው ብዙ ነው እግዚአብሔር ግን ከሁሉም ያድነዋል ይላል (መዝ.34፡1፣19) ።

ይሄ የአመስጋኝነት ሀይል ነው፡፡ ነጻ ለመውጣት ብቻ አይደለም የሚረዳን ነገር ግን ቆም ብለን እግዚአብሔርን በህይወታችን ስላገኘናቸው በረከቶች ስናመሰግነው ሌሎች በረከቶችን ማግኘት እንቀጥላለን፥ ሌላ የማመስገኛ ምክንያት ማለት ነው!

አመስጋኝነትን ለመለማመድ ጊዜን እንድትወስዱ አበረታታችኋለሁ፡፡ ልናመሰግንበት የሚገባን ብዙ ነገር አለ፤ በእያንዳንዱ ዕለት ልናተኩርበት ይገባል፡፡…አመስግኑት፣ ስሙንም ባርኩ የሚለውን የመዝሙረኛውን ምክር አትርሱ! (መዝ.100፡4) ።


የጸሎት መጀመሪያ

ውድ እግዚአብሔር ሆይ የአመስጋኝነት ሀይል በእውነት አስገራሚ ነው፡፡ በየዕለቱ ስለምትባርከኝና በህይወቴ ስራን ስለምትሰራ አመሰግንሀለሁ፡፡ ያለ አንተ ምንም እንደሌለኝ አውቃለሁ፡፡ ስላሳየኸኝ መልካምነት አመሰግናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon