አስተሳሰብህ እስኪለወጥ ድረስ ሕይወትህ አይለወጥም

በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፡፡ – ፊል 4፡8

እኔ ደስተኛ ሳልሆን ብዙ ዓመታትን አሳልፌአለሁ ምክንያቱም በየማለዳዉ ስነቃ የማስበዉ አሉታዊ ነገር ፣ ሐዘን እና የሚያስደብሩ ነገሮችን ነዉና፡፡ አሁን ግን መንፈስ ቅዱስ እንዴት በክርስቶስ ልብ መመላለስ እንዳለብኝ ረድቶኝ ሙሉ በሙሉ የረካሁ ነኝ ማለት እችላለሁ፡፡

ምንአልባት እንደእኔ ትክክል ያልሆኑ ነገሮችን በማሰብ ዓመታትን ፈጅተህ ሊሆን ይችላል፡፡ መልካሙ ዜና ግን በእግዚአብሔር እርዳታ ነገሩ ዛሬ ሊለወጥ ይችላል፡፡

ከአሉታዊ አስተሳሰቦች ጋር እየታገልህ ከሆነ፤ አስተሳሰብህ ሳይለወጥ ሕይወትህ አይለወጥም የሚለዉን እዉነት አጥብቀህ መያዝ ይገባሃል፡፡ የተለወጠና እግዚአብሔራዊ አስተሳሰብ ለለወጥ ወሳኝ ነዉ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ዓይነት ነገሮችን ማሰብ እንዳለብን የሚናገርበት ብዙ ክፍል አለዉ፤ ፊልጵስዩስ 4፡8 ስለሚገነቡ እንጂ ስለሚያፈርሱ ነገሮች እንዳናስብ ይናገራል፡፡

ዛሬ ልገዳደርህ እፈልጋለሁ፤ በማለዳ ነቅቶ አሉታዊ ነገር እያሰቡ በመሄድ ፈንታ ከመጽሐፍ ቅዱስ አዉንታዊ ነገር ምረጥና በየዕለቱ ስትነቃ በእርሱ ላይ አተኩር፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በዉስጥህ ይደግ ፣ አእምሮህንም ይቀይር፡፡ አእምሮህን በመልካም ነገሮች ላይ አድርግ ከዚያም በሚመጣዉ ለዉጥ ተደሰት፡፡

ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በክርስቶስ ልብ ልለወጥና ልኖር ዝግጁ ነኝ፡፡ እውነተኛ የሆነውን ነገር፣ ጭምትነት ያለበትን ነገር፣ ጽድቅ የሆነውን ነገር፣ ንጹሕ የሆነውን ነገር፣ ፍቅር ያለበትን ነገር፣ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር፣ በጎነት እንዳስብ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon