
ኃጥያተኛ መቶ ጊዜ ክፉን ቢሠራ ዘመኑን ረዥም ቢሆን እግዚአብሔርን ለሚፈሩት በፊቱም ለሚፈሩት ዳኝነት እንዲሆን አውቃለሁ፡፡ መክ 8÷12
እግዚአብሔር ስለ አስተዳደራዊ በደል በጣም ጠቃሚ ትምህርት አስተማረኝ፡፡ ኢየሱስ አለ ‹‹ወደ እኔ ኑ›› ማቴ 11፡ 28፣ እርሱ ወደ ስልክ ሩጡና በአደጋ ጊዜ ሊረዱአችሁ ወደሚችሉ ሶስት ጓደኞቻችን ጥሩ አላለም፡፡ እኔ ሰዎች እንዲፀልዩልን መጠየቃችንን እየተቃወምኩ አይደለም፡፡ ነገር ግን ወደ ሰው ብንሮጥ የቁስልን ፈውስ ሳይሆን ምናልባት ቁስላችንን ያሽጉልን ይሆናል፡፡
በሕይወታችን ብዙ ችግሮችን ኪሳራ ሊገጥመን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ኪሳራዎች ታልቅ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቀላል ሊሆን ይችላል፡፡ ተደጋጋሚና ተከታታይ በሆነ የሕይወት አደጋ ሥር ላለመኖር ጌታ እርሱን በመፈለግ እንዲተጋና በፈለገው እንዲቀጥል አነቃኝ፡፡ በፊት ሲያስፈልግና በችግር ጊዜ ብቻ ጌታን እፈልገው ነበር፡፡ ውሎ አድሮ ግን ከኪሣራ የሕይወት አሠራር ዘዴ እንዲወጣ ጌታ አስተማረኝ፡፡ ጌታን በማንኛውም ጊዜ ማለት ተስፋ በሚያስቆረጥ ሁኔታም ይሁን በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ገጠመኞች ጊዜም ሆነ እንዲሁም በስኬትና በታላቅ በረከትም ወቅት መፈለግን ተምሬያለሁ፡፡
እኛ አብዛኛውን ጊዜ ነገሮቻችን መልካምና በጥሩ ሁኔታ ሲጓዙልን ለጌታ ያለን ቅድሚያ ዝቅ ይላል፡፡ እኔ እንዳስተዋልኩት ከሆነ እኛ እግዚአብሔርን በችግርና ደስ በማይለን ጊዜያት በጣም የምንፈልገው ከሆነ እግዚአብሔር ሁልጊዜ በዚያ ሁኔታ ውስጥ በመቆየት ማለት በአስቸጋሪና ደስ በማያሰኝ ሁኔታ ውስጥ በመሆን የእርሱን ሕብረት እንድናጠብቅ ልያደርግ እንደሚፈልግ እንደሆነ ነው፡፡
እግዚአብሔር እኛ ወደ እርሱ ለእርዳታ ስንመጣ ሁልጊዜ ከአደጋ እየተጠቀና ይረዳናል፡፡ ነገር ግን እኛ ቀጣይነት ባለው በሠላምና በድል ሕይወት ውስጥ መሰንበት ከፈለግን እግዚአብሔርን በተከታታይነትና በቀጣይነት፣ ሁልጊዜ በሁሉም ሁኔታ ውስጥ የዛሬው ጥቅስ እንደሚያስረዳን እርሱን መፈለግ አለብን፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ከእግዚአብሔር ጋር በሕብረት ወዳጅነትህን ሁልጊዜ በማሳለፍ ጥሩ አስተዳደራዊ ኪሳራን ተለማመድ፡፡