አቅማችሁን አሳድጉ እና አሁን አንድ ነገር አድርጉ

አቅማችሁን አሳድጉ እና አሁን አንድ ነገር አድርጉ

የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉት ቆጥራችሁ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት… – ቆላ 3፡23

እግዚአብሔር ከታላቅ አቅም ጋር እንደፈጠራችሁ ታውቁ ይሆናል፣ ነገር ግን እዛ ጋር ማቆም የለባችሁም።አቅማችሁን ማዳበር ይገባችኋል፡፡

ብዙ ሰዎች አቅማቸውን ለማዳበር ምንም ነገር እያደረጉ ካልሆነ ደስተኛ አይደሉም ብዬ አስባለሁ፡፡አቅማችሁ በሙሉ መልኩ ሲያድግ ማየት ከፈለጋችሁ፥ ሁሉ ነገር እስኪስተካከል ድረስ አትጠብቁ፡፡አሁን አንድ ነገር አድርጉ፡፡ፊት ለፊታችሁ ባለው ማናቸውም ነገር ላይ እጃችሁን ጫኑ፡፡

በእርሱ ተጠቅማችሁ የሆነ ነገር በመስራት ብቃታችሁን የሆነ ቅርጽ ልታስይዙት ይገባል፡፡አዳዲስ አጋጣሚን የመጠቀም መሻት በልባችሁ ውስጥ ካለ፥ እግዚአብሔር ያንን እንድታደርጉት ስጦታን ሰጥቷችሁ ይሁን አይሁን ውጡና ሞክሩት፡፡ምንም ነገር ለማድረግ የማትሞክሩ ከሆነ ችሎታችሁን መቼም አታውቁትም፡፡

ብቃታችሁን ለማዳበር የእምነት እርምጃን ስትራመዱ ፍርሀትን እንድትቋቋሙት አበረታታችኋለሁ፡፡የእግዚአብሔር ፍጹም ፍቅር ፍርሀትን አውጥቶ ስለሚጥል በመሳሳት ፍርሀት ተሸመድምደን መኖር የለብንም፡፡በለመዳችሁት የምቾት ቅጥር ውስጥ መኖር ደህንነት እንዲሰማችሁ ቢያደርግም ነገር ግን አቅማችሁን በማሳደግ ውጤታማ መሆን ወይም በምትሰሩት መከናወን አትችሉም፡፡ስለዚህ እግዚአብሔር እንድታደርጉት እየመራችሁ እንደሆነ በሚሰማችሁ ነገር ላይ እርምጃን ለመውሰድ ቁርጠኛ ውሳኔን አሳልፉ፡፡

ከእግዚአብሔር በተሰጠ ብቃት የተሞላችሁ ናችሁ እናም በህይወታችሁ ውስጥ ከምታስቡት በላይ ነገሮችን ማድረግ ይፈልጋል፣ ግን የእናንተን ትብብር ይፈልጋል፡፡በሙሉ ልባችሁ ውጡናዛሬውኑ አገልግሉት፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ በማደርገው ነገር ሁሉ በሙሉ ልቤ ላገለግልህ እፈልጋለሁ፡፡የሰጠኸኝን ታላቅ ብቃት በማዳበር ወጥቼ እርምጃ እንድወስድ ስላበረታታኸኝ አመሰግንሀለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon