
ኢየሱስም አያቸውና፣”ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤በእግዚአብሔር ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም፤በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላል” አላቸው፡፡ – ማር 10፡27
በጣም የሚገርመው ሰንት ስጦታ ያላቸው ብዙ ሰዎች በህይወታቸው ላይ ምንም ሳያደርጉ ዳር ይዘው መቀመጣቸው ነው። እግዚአብሔር የለገሳቸውን ተሰጥኦ ለመጠቀም ወደፊት እርምጃ አይወስዱም፣ ምክንያቱም መጀመሪያውንም ያ ተሰጥኦው እንዳላቸው አያምኑም፡፡ከእነርሱ አንዱ ናቸሁ?
እውነቱ ግን፥ እግዚአብሔር ለሁላችንም ስጦታዎችን፣መክሊቶችን እና ችሎታዎችን ሰጥቶናል፡፡ለእናንተ ታላቅ እቅድ አለው፣ እናም ለመንግስቱ ታላላቅ ነገሮችን እንድትሰሩ በታላላቅ ተሰጥኦዎች አስታጥቋችኋል፡፡ነገር ግን እርሱ እንደሚያያችሁ ራሳችሁን ማየት እስክትጀምሩ እና ስጦታዎቻችሁን እንድትጠቀሙባቸው እንደሚያስችላችሁ እስክታምኑበት ድረስ እግዚአብሔር በሰጣችሁ አቅም ልክ መኖር አትችሉም፡፡
ከአነስተኛ በራስ የመተማመን ስሜት፣ስለራሳችሁ ባለ ደካማ የራስ እይታ፣ እናም ከድፍረት እጥረት ጋር እየታገላችሁ ካላችሁ እግዚአብሔር ከሚደንቅ ብቃት ጋር እንደፈጠራችሁ እንድታውቁ እፈልጋለሁ፡፡እግዚአብሔርን ስትታመኑት እና ልታደርጉ ትችላላችሁ ብሎ ያመነባችሁንን ነገር ሁሉ እችላለሁ ብላችሁ ስታምኑ፥ ለህይወታችሁ ያሰበላችሁን እጣፋንታችሁን ታሳካላችሁ፡፡
አስታውሱ “ለእግዚአብሔር ሁሉ ይቻላል፡፡” ድፍረታችሁን በእርሱ ስታደርጉት ከአቅማችሁ በላይ ለመኖር ነጻ ትሆናላቹሁ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ ራሴን በአንተ አይኖች ከሰጠኸኝ ስጦታዎች እና መክሊቶች ጋር እንዳይ እርዳኝ፡፡የፈጠርከኝ ከብዙ አቅሞች ጋር ነው ብዬ አምናለሁ ምክንያቱም አንተ ታላቅ አምላክ ነህ፡፡ዛሬ መተማመኔን በአንተ ላይ አድርጌ ሁሉም ነገር በአንተ እንደሚቻል አምናለሁ፡፡