ሕልም በስራ ብዛት ይታያል ፤ እንዲሁም የሰነፍ ድምጽ በቃሉ ብዛት ይሰማል፡፡ – መክብብ 5፡3
ፍሬ በማያፈራ ነገር እየተጨነክ እየዳከርክ ነው? የስራ ብዛት ይሆን ሰላምህን የሰረቀው?
በእንግሊዝ ሀገር የበኪንግሃም ፓላስ ጥበቃ ስለነበረ አንድ የመሬት ጠባቂ ሰው የሰማሁት ነገር ነበር ፤ ይህ መሬት ለ 100 ዓመታት ፣ ለሃያ አራት ሰዓታት የሚጠበቅ ነበር፡፡ በመጨረሻም አንድ ሰው ‹‹ምንድን ነው የምትጠብቀው? ››በሎ ጠየቀው ጠባቂውም ምን እንደሚጠብቅ አላወቀም ፤ ላለፉት 100 ዓመታት ሲጠበቅ ነበር ብሎ መለሰ፡፡
የዛሬ 100 ዓመት ገደማ ንግስቲቱ የቀያይ ጽጌረዳዎችን ችግኝ አስተክለው ነበር ፤ ማንም እንዳይረግጠው እና እንዲያድጉ አሳስበውን ነበር ፤ ከአንድ ክፍለዘመን በኋላ ጠባቂው ጽጌረዳ የሌበት መሬት እየጠበቀ ይገኛል፡፡
ለምን እንድምታደርጉት አታውቁም ግን እያደረጋችሁት ያለ ነገር አለ ? በስራ ብዛት ውጥረት ውስጥ እንድንገባ እግዚአብሔር አልጠራንም፡፡ ፍሬያማ እንድንሆን ተጠርተናል፡፡ የማይረቡ ነገሮች ውጥረት ከመጨመራቸው ውጭ ምንም ምርታማ አያደርጉንም፡፡
በየቀን ምን ስትሰሩ እንደምትውሉ ቆም ብላቸው እስኪ መርምሩ ፤ ምናልባት እግዚአብሔር አድርጉ ያላላችሁን ነገር ስታደርጉ ትውሉ ይሆናል ወይም አድርጉ ያላችሁን ስታደርጉ ነበር ፤ አሁን ግን ያ ነገር ላይኖር ይችላል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ፍሬ ከማይገኝበት መጨነቅ አውጥቶ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩ ይርዳችሁ፡፡
ጸሎት ማስጀመሪያ
መንፈስ ቅዱስ ሆይ ሕይወቴን እንደመዝን እና ዝባዝንኬ ነገሮች ቆርጬ እንድጥል እርዳኝ ፡፡ በፍጽም ባተሌ መሆን አልፈልግም፡፡ ፍሬያማ የምሆንበትን ሕይወት አሳየኝ፡፡