አትፍራ መንፈስ ቅዱስን ተከተል

አትፍራ መንፈስ ቅዱስን ተከተል

እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ። – ት.ኢሳ 41፡10

ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ደፋር ለመሆንና በመንፈስ ቅዱስ ለመበርታት ትልቅ ማበረታቻ ነዉ፡፡ አንዳንዴ ያለ እግዚአብሔር ፈቃድና ከጊዜዉ ዉጪ የሆነ ነገር አንፈልግም ግን ደግሞ እግዚአብሔር ሲንቀሳቀስ ለመንቀሳቀስ መፍራት የለብንም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ወደ አዲስ አቅጣጫ ሊመራን ሲጀምር ሰይጣን ወደ አእምሮአችንና ስሜታችን ፍርሃት ያመጣል፡፡ ወደ እግዚአብሔር ከመንቀሳቀስ ሊያግደን ፍርሃትን ይጠቀማል፡፡

ኢሳያስ 41፡10 የሚለዉ እኔ ካንተ ጋር ነኝና አትፍራ ነዉ፡፡ በንድ ነገር ከፈራክና ከፍርሃት ነጻ መሆንን ከፈለግህ ከፍርሃት ጋር የምትጋጠምበት ጊዜ ይመጣል ያኔ ወደ ኋላ እንዳትመለስ፤ የኢየሱስን እጅ ያዝ እርሱ አብሮህ እንዳለ እወቅ እናም አድርግ፡፡ እርሱ ከአንተ ጋር ስላለ አትፍራ፡፡

ከእነዚህ በአንዱ መስቀለኛ መንገድ ካለህ ወደ ፊት እንድትሄድ አበረታታሃለሁ፡፡ አትሸበር ግን እጁን ይዘህ ወደ ፊት ተጓዝ፡፡ አስተዉል እግዚአብሔር ከፍርሃቶችህ ሁሉ ነጻ ሊያወጣህ ይፈልጋል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ አንተ ወደ ምትመራኝ ወደ የትም ልከተልህ እፈልጋለሁ ፤ ከአንተ ጋር ወደ ፊት መጓዝ እችል ዘንድ ደፋር አድርገኝ እርዳኝም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon