አንከባልላቸው

አንከባልላቸው

የምታደርገውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤ ዕቅድህም ሁሉ ይሳካልሃል። (ምሳሌ 16 3)

ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ወዳጅነት መመሥረት ከፈለግለግን ደግሞም በታማኝነት ለእርሱ የምንኖር ከሆነ ስለራሳችን ሁሉንም ነገር ወስደን እንዲህ ልንለው ይገባል። “እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህንን ለአንተ እሰጥሃለሁ። ይህንን ችግር እሰጥሃለሁ። ይህንን ሁኔታ እሰጥሃለሁ። ይህንን ግንኙነት እሰጥሃለሁ። ሙሉ በሙሉ ለእንተ እተወዋለሁ። ለእኔ በጣም ብዙ ነው። መጨነቄን እና ሁሉንም ነገር ለማስተካከል መሞከሬን አቆማለሁ – እናም በአንተ ላይ እጥለዋለሁ። አምላኬ ሆይ ራሴንም ለአንተ እሰጠሃለሁ ምክንያቱም ስለራሴ ምንም ማድረግ አልችልም። ሁሉንም ለአንተ እሰጥሃለሁ። ብርታቴን እና ድካሜን እሰጥሃለሁ። መለወጥ እፈልጋለሁ፣ ልትለውጠኝ ያስፈልጋል።” በመጨረሻም እኔን መለወጥ የእግዚአብሔር ሥራ መሆኑን የእኔ ሥራ ደግሞ ማመን መሆኑን ስገነዘብ ለእኔ ታላቅ ቀን ነበር!

መዝሙር 37፡5 “መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ በእርሱም ታመን እርሱም ያቀናልሃል” ይላል። መንገዶቻችንን ለእግዚአብሔር አደራ መስጠት ማለት ምን ማለት ነው? ከራሳችን ላይ “ማንከባለል” እና በእርሱ ላይ ማድረግ ማለት ነው። ችግሮቻችንን እና ሰውኛ ምክንያቶቻችንን ወደ እግዚአብሔር ስናንከባልል፣ ይህም ማለት ሙሉ በሙሉ በእርሱ ላይ መታመን ማለት ነው፣ ከዚያ እሱ ሀሳባችንን ይለውጣል ደግሞም ከፈቃዱ ጋር እንዲስማሙ ያደርጋቸዋል። በሌላ አገላለጽ እርሱ የሚፈልገውን እንድንፈልግ የእርሱ ሀሳቦች የእኛ ሀሳቦች ይሆናሉ። ያ በሚሆንበት ጊዜ፣ እቅዶቻችን ከእግዚአብሔር እቅዶች ጋር ሙሉ በሙሉ ስለሚስማሙ ስኬታማ ይሆናሉ። እግዚአብሔር ሲናገርህ መስማት እንድትችል እራስህን እና የያዝከውን ሁሉ ልቀቅ እና ዘና በል።


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ችግሮችህን ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ አንከባልል።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon